Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
በጉባኤ የሚነገር የጸና የቀና የጎላ የተረዳ ሃይማኖት ት በተዋህዶ ከበረ ነው። ዛሬም አውጻእኩከ አንሣእኩከ ሲል ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጽሐፍን ገልጦ አነበበ ይላል ያነበበው ቃልም ይህ በኢሳይያስ ትንቢት ተጽፎ ያለውን ቃል ነውና ትርጓሜው ተመሳሳይ ነው። ጥምቀት አንዲት ናት ስንል አጥማቂው ሥልጣነ ክህነት የሌለው ሰው ቢያጠምቅ ያ እንደ ጥምቀት አይቁጠርም ምክንያቱም ልጅነትን አያስገኝምና ነው። ስለዚህ ልጅነትን ለማግኘት አማኒ ለመኾን በተዋሕዶ ሥርዓት ጥምቀት ሊፈጸምለት ይገባል ማለት ነው።
ኢትዮጵያን ግራኝ አህመድ በወረራት ጊዜ ዐፄ ልብነ ድንግል ከፖርቹጊዝ መንግሥት እርዳታ ጠይቀው እርሳቸው ከሞቱ በኋላ በፖርቹጊዞች እርዳታ ግራኝ ድል ሆኖ ኢትዮጵያ ሙሉ ነጻነቷን አግኝታ መንግሥቷን በትክክል ማቋቋሟ የታወቀ ነው በዚህ ጊዜ ከኢትዮጵያ ተልኮ ፖርቹጊዞችን ለእርዳታ ያመጣው ቤርሙዲዝ ደ ከኢትዮጵያ ግዛት ገሚሱ ለፖርቹጊዝ መንግሥት ይሰጥ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ከእንግዲህ ወዲያ አቡን ከእስክንድርያ መምጣቱ ቀርቶ ከሮም ይምጣ እኔም ለኢትዮጵያ አንደኛ መጀመሪያ ሮማዊ ጳጳስ ልሁን ብሎ ዐፄ ገላውዴዎስን ጠየቀ ዐፄ ገላውዴዎስም ሊቃውንቱን ሰብስበው ምን እናድርግ ብለው ጠየቁ የኢትዮጵያ ሊቃውንትም ፍርድ በቃ ይስጡን እንከራከርና ሮማውያን ቢረቱን እንልቀቅላቸው ብንረታቸው ይልቀቁልን አሏቸው ንጉሁም ፈቅደው ጉባዔ ተደረገ ለኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጉባኤ ዝክሪና ጳውሊ ኾኑ ዝክሪና ጳውሊም በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጠገብ የሚገኝ የደብረ ጽሙና ገዳም ሊቃውንት ናቸው ኢትዮጵያውያን ሮማውያንን ሀገራችሁ ወዴት ነው ሃይማኖታችሁ ምንድን ነው ሲሉ ጠየቋቸው ሮማውያን ሲመልሱ ሀገራችን ሮም ነው ሃይማኖታችንም ኹለት ባሕርይ ኹለት ጠባይዕ አንዱ የመለኮቱ አንዱ የትስብእቱ እንላለን ኹለተኛም ወልድ ከአብ ያንሳል መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል እንላለን አሏቸው ኢትዮጵያውያን ሲመልሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ የሚል ምን አለ እስኪ አስረዱን አሏቸው ሮማውያን ሲመልሱ እርሱው ራሱ ወልድ ደቀመዛሙርቱ ሕልፈተ ዓለም የሚሆነው መቼ ነው ብለው ቢጠይቁት መላእክትም ቢሆኑ ወልድም ቢሆን ከአብ በቀር ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የሚያውቃት የለም ብሏል ስለዚህ አብ መለኮት ስለሆነ ያውቃል ወልድ መንፈስ ቅዱስ ግን መለኮት ስላልሆኑ አያውቁም እንላለን እናንተ ይህን ነገር ምን ትሉታላችሁ አሉ አባ ዝክሪ ሲመልስ ሦስቱን አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን አንድ አምላክ የምንላቸው አብን ልብ ወልድን ቃል መንፈስ ቅዱስን እስትንፋስ ብለን በአብ ልብነት ያስባሉ ያውቃሉ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ እስትንስነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ ለየራሳቸው ልብ ቃል እስትንፋስ የላቸውም በማለት ነው ልብ ቃል እስትንፋስ ያለው አንድ ሰው በልቡ አስቦት አውቆት ለመናገር ጊዜው ባለመድረሱ ሰዓት እየጠበቀለት ሰውሮ የያዘውን ነገር ጊዜው ባለመድረሱ ምክንያት በቃሉ ሳይናገረው ቢቆይ ቢጠየቅም ዛሬ አልናገረውም ቢል አያውቅም እንደማይባል ወልድም ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የምትገለጽበት ጊዜው እስኪደርስ በልቤ በአብ ሰውሬ አቆያታለሁ እንጅ ዛሬ በቃልነቴ አውጥቼ አልናገራትም ማለቱ ነው እንጅ የማያውቃት ሆኖ አይደለም እንዲህስ ባይሆን የከዊን ስማቸውና ግብራቸው ተፋልሶ አብ ቃል ወልድ ልብ በተባሉ ነበረ አለው በዚህ ጊዜ ሮማውያን መልስ አጥተው ዝም አሉ ኹለተኛ ጥያቄ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሮማዊ ተነሥቶ መለኮት ሥጋ አልሆነም ሥጋም መለኮት አልሆነም ሥጋ ለመለኮት እንደ ብረት ልብስ እንደ ጥሩር ኾነው መለኮትና ሥጋ እንደ ኀዳሪና ማኅደር ኾነው መለኮት የመለኮትን ሥራ ትስብእትም የትስብእትን ሥራ ሲሰሩ ኖረው በዕርገቱ ጊዜ የለበሰውን ሥጋ አውልቆ በሦስተኛው ሰማይ አኑሮት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀመጠ የዚህም ምሳሌው አንድ ንጉሥ ለጦርነት ወደ ሰልፍ ሲገባ የጦርነት ልብስ ይለብሳል ሲዋጋ ውሎ ድል ካደረገ በኋላ የለበሰውን የጦር ልብስ አውልቆ ከግምጃ ቤት ሰቅሎ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ እንደሚቀመጠው ያለ ነው እንጅ ትስብእቱን ከመለኮቱ ጋራ በአባቱ ቀኝ አያስቀምጠውም አለ አባ ዝክሪ ሲመልስ ነፍስ ርቀቷን ሳትለቅ ሥጋ ግዙፍ ውሱን መኾኑን ሳይለቅ ተዋሕደው አንድ ሰው እንዲኾኑ መለኮት ምልዐቱን ስፍሐቱን ርቀቱን ሳይለቅ ትስብእትም ግዙፍነቱን ውሱንነቱን ሳይለቅ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኾኗል እንጅ እንደ ልብስና እንደ ገላ አይደለም አለ ሮማዊ መለኮት ከደረሰበት ኹሉ ይህ መዋቲ ትስብእት ደረሰ ትላለህን አለ አባ ዝክሪ ሲመልስ እኔስ መለኮት እና ትስብእት በተዋህዶ አንድ ስለሆኑ መለኮት በሥጋ ውሱን ግዙፍ ኾነ ትስብእትም በመለኮት ምሉዕ ስፉሕ ረቂቅ ኾነ እላለሁ ትስብእት ከመለኮት ተለይቶ በሦስተኛው ሰማይ እንዳልቀረ በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ እንደተቀመጠም ሲያስረዳ አሜሃ ትሬእይዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው እንዘ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ብሏል በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም እንዲመጣ ሲያስረዳም ወአመ ይመጽእ ወልደ እጓለ እመሕያው በስብሐተ አቡሁ ወኩሎሙ መላእክቲሁ ምስሌሁ ብሏል ይህ ንባብ በቅዱስ ወንጌል መጻፉን ታምናለህ ትክዳለህ። አለው ሮማዊ መልስ አጥቶ ዝም አለ ሦስተኛ ጥያቄ ሮማዊ እኔ ክርስቶስን ፍጡር እለዋለሁ አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ክርስቶስን ፍጡር የሚል ንባብ ከምን ታገኛለህ አለው ሮማዊ አምላክ ከኾነ ከሣምራዊት ውኃ እስኪለምን ድረስ ለምን ተጠማ ከላይ ያለው ሐኖስ ከታች ያለው ውቅያኖስ በመኃል እጁ ሲሆን አምላክ ይጠማልን አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ፍጡር ከኾነ የእግዚአብሔርንስ ስጦታ አውቀሽ ቢኾን ይህ ውኃ አጠጭኝ ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደሆነ ተገንዝበሽ አንች የሕይወት ውኃን አጠጣኝ ብለሽ በለመንሺው ነበረ እርሱም በሰጠሸ ነበረ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ኹሉ ዳግመኛ ይጠማል እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ዳግመኛ ይህ እኔ የምሰጠው ውኃ ለዘላለም ሕይወት ሊኾነው ከውስጡ ሲመነጭ ይኖራል እንጅ ዳግመኛ አይጠማም ለምን አላት አለው ዐራተኛ ጥያቄ ሮማዊ አምላክ ከኾነ አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት ብሎ ለምን ጠየቀ የተቀበረበትን ባላወቀውም ነበረን ኹለቱ ዕውራንስ የዳዊት ልጅ ይቅር በለን ባሉት ጊዜ ምን ትሻላችሁ ብሎ ለምን ጠየቃቸው የሚሹትን ባላወቀውም ነበረን አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ እግዚአብሔር አዳምን አይቴ ሀሎከ ብሎ ጠየቀው ይላል ዘፍ ርፎ ሙሴንም ምንት ውስተ እዴከ ብሎ ጠየቀው ይላል ዘፀ ጀ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ መጠየቁ አዳም ያለበትን ቦታ አጥቶት ሙሴም በእጁ ምን እንደያዘ አላውቀው ብሎ ይኾን አይደለም ይህም ይህን የመሰለ ጥያቄ ነው በዚያውስ ላይ ፍጡር ከኾነ አልዓዛር አልዓዛር ነዓ ፃዕ አፍአ እመቃብር ብሎ ሊያስነሣው እንደምን ቻለ በደረቅ ግንባርስ ላይ ዐይን ሊፈጥር እንደምን ቻለ አለው ሮማዊ ይህን የመሳሰለስ ቅዱሳንም ልዩ ልዩ የኾኑ ብዙ ተአምራት ያደርጋሉ አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ቅዱሳን ልዩ ልዩ ተአምራት ቢያደርጉ የርሱን ስም ጠርተው በስሙ ለኢየሱስ ናዝራዊ ተንሥእ ወሑር እያሉ ነው ግብ ሐዋ ጀቿ እርሱ ግን እኤዝዘከ ፃዕ እምኔሁ እያለ በገዛ ሥልጣኑ ነውና ቅዱሳን ከሚያደርጉት ተአምራት ጋራ ሊነጻጸር አይገባውም አለ በዚህ ጊዜ ሮማዊ መልስ አጥቶ ዝም አለ ዐምስተኛ ጥያቄ ስሙን ልዮን የሚሉት አንድ ሮማዊ ተነሥቶ ወልደ አብ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሥጋ ማርያምን በለበሰ ጊዜ ሰይፍ በሰገባው እንዲከተትና እንዲቀመጥ አደረበት እንጅ አልተዋሐደውም በሰላሳ ዘመኑ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በራሱ ላይ ሲቀመጥ መለኮቱ ከትስብእቱ ተዋሐዶ የጸጋ አምላክ ኾነ መዋቲ ትስብእትም የማይሞት ኾነ ከሰላሳ ዘመን በፊት የጸጋ አምላክ ስላልኾነ አምላካዊ ሥራ አልሠራም ከተጠመቀ በኋላ ግን የጸጋ አምላክ ስለኾነ ውኃውን ወይን አደረገ ብዙ የአምላክነት ሥራ ሠራ አለ እንደዚኸውም በንግድ ምልክት መጥቶ እስክንድርያዊ መስሎ በኢትዮጵያ የሚኖር አንድ ሰው ተነሥቶ እንዲህ ሲል ተናገረ እናንተ ኢትዮጵያውያን ቃል ሥጋ በለበሰ ጊዜ በማኅጸነ ማርያም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የባሕርይ አምላክ ኾነ ትላላችሁ በማኅጸን መንፈስ ቅዱስን ሲቀበል ያየው የለም ሮማውያን ግን እስከ ሰላሳ ዘመን በሰብአዊ ግብር ኖሮ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ ሰው ሁሉ እያየው በራሱ ላይ ስለተቀመጠበት የጸጋ አምላክ ኾኖ የአምላክነት ሥራ ሠራ ይላሉና ከእስክንድርያ ሃይማኖት የሮማ ሃይማኖት ትሻላለች አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ሲያበሥራት መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል የአብም ኃይሉ ይጋርድሻል ካንች የሚወለደውም ቅዱስ ነው የልዑል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ብሎ ሦስቱም አካላት በማኅጸነ ማርያም እንደ አደሩ ተናግሯል ማደራቸውም አብ ለአጽንዖ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ ወልድ ለለቢሰ ሥጋ ነው እንጅ ሦስቱ ኹሉ ለለቢሰ ሥጋ ያደሩ አይምሰልህ በዚህ ጊዜ መለኮት ርቀቱን ለቆ ሳይገዝፍ ሳይለወጥ ትስብእትም ግዘፍነቱን ለቆ ሳይረቅ ሳይለወጥ እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኾነ ወልድ ለለቢሰ ሥጋ ማለት ይህ ነው አብ ለአጽንዖ ማለትም ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ምሉዕ ስፉሕ ረቂቅ መለኮትን እመቤታችን በጠባብ ማኅጸን እንድትችለው አጸናት ማለት ነው መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ ማለትም ትስብእትን ከአዳም መርገም አንጽቶ ቀድሶ ለተዋሕዶተ መለኮት የበቃ አደረገው ማለት ነው ይህን በማኅጸን በረቂቅ ምሥጢር የሠሩትን አምላካዊ ሥራ በዮርዳኖስ ወልድ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ሲጠመቅ በመታየት አብ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ የሚል ድምጽ በማሰማት መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀምጦ አብ ልጀ ይህ ነው ብሎ የመሰከረለት ወልድ ይህ ነው ብሎ በጣት ጠቅሶ እንደ ማሳየት በመመስከሩ ገልጸውለታል እንጅ እስከዚያ ድረስ ሰላሳ ዘመን መንፈስ ቅዱስ ተለይቶት ኖሮ በዮርዳኖስ አደረበት ማለት አይደለም አለ ያ ሮማዊ መልስ አጥቶ ዝም አለ በዚህ ጊዜ ንጉሁ ገላውዴዎስ አባ ዝክሪንና አባ ጳውሊን እኔ የክርስቶስ ባሪያ ሃይማኖቴ እንደ ሃይማኖታችሁ ኦርቶዶክስ እስክንድርያዊ ነው ይህነንም እናንተ ታውቁልኛላችሁ ነገር ግን እኛ የሕክምናና የተግባረ እድ ትምህርት የለንም ሮማውያን ብዙ ጥበብ ያውቃሉና ይህን ጥበባቸውን እስኪያስተምሩን ድረስ በሀገራችን እንዲቆዩ ፈቃዳችሁ ይኹን ሲል ለመናቸው አባ ዝክሪ የተባለው መነኩሴ ተነሥቶ እናንተ የኢትዮጵያ ሰዎች እሊህ ሮማውያን በሀገራችን ይቀመጡ ካላችሁ ወደፊት በኢትዮጵያ ላይ የሚደርስባትን ነገር ልንገራችሁ እኒህ ሰዎች ከእህቶቻችን ከልጆቻችን ይወልዳሉ እኒያ ልጆች በድብቅ ያባቶቻቸውን የካቶሊካውያንን ትምህርት ይማራሉ እኛ ወገኖቻችን መስለውን ቅስና ዲቁና ስንሾማቸው የመምህርነት ማዕርግ ስንሰጣቸው ውስጥ ውስጡን የኹለት ባሕርይን ባህል እያስተማሩ ሃይማኖታችንን ይለውጧታል ይህም የተናገርኩት ነገር አይቀርም አምስት ነገሥታት ካለፉ በኋላ ስድስተኛ ንጉሥ ከወደ ዐረማውያን ሀገር መጥቶ ይነግሣል በርሱ ጊዜ ይፈጸማል ሲል ትንቢት ተናገረ ከዚህ በኋላ ከዐፄ ገላውዴዎስ ዐፄ ፋሲል ከዐፄ ፋሲል ዐፄ ሚናስ ከዐፄ ሚናስ ዐፄ ሠርጸ ድንግል ከዐፄ ሠርጸ ድንግል ዐፄ ያዕቆብ ከዐፄ ያዕቆብ ዐፄ ሱስንዮስ ዐፄ ሱስንዮስ ከዐረማውያን ሀገር መጥተው ነገሠ በስድስተኛው ንጉሥ በዐፄ ሱስንዮስ ጊዜ የአባ ዝክሪ ትንቢት ተፈጸመ ሜስ እና የተዋሕዶ ልዩነት ክፍል የኢትዮጵያ ሊቃውንት ከሚሲዮናውያኑ ጋር ባደረጉት ክርክር ሚሲዮናውያኑ ለጊዜው የተሸነፉ መስለው ከክርክሩ ራሳቸውን አሸሹ ከዐጹ ገላውዴዎስ ሞት በኋላ በተሾሙት በወንድማቸው በዐጹ ሚናስ ዘመነ መንግሥትም እንዲሁ ክርክር አድርገዋል በእነዚህ ዘመናት ሁሉ እምነታቸውን በድብቅ ያስተምሩ ነበርና ንጉሁ የሚሲዮኖችን ፓትርያርክ ኦቢያዶን አስጠርተው ድጋሜ የካቶሊክን እምነት እንዳያስተምር አስጠነቀቁት እጸድቅ ብየ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች እንደሚባለው ሆኖ ኦብያዶ በዚህ የተነሣ የንጉሁሥን ሥም ማጥፋት እና ከእስላሞች ጋር በምሥጢር እየተገናኘ ንጉውን ለማስገደል እንዲሁም የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ለማስያዝ ወጥመዱን ያጠምድ ጀመረ ይህ ክፉ ሥራው ስለታወቀ ከጓደኞቹ ጋር ተይዞ በግዞት ተቀመጡ ሆኖም ግን ከዚህ አምልጠው በኢትዮጵያ ዙሪያ ከሰፈሩት ጠላቶቻችን ከቱርኮች ጋራ ተቀላቀሉ ሚሲዮኖቹ ግን የካቶሊክ እምነትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ቆርጠው ተነሥተዋልና ብዙ አማራጮችን ተጠቅመዋል ከዐጹ ሚናስ ሞት በኋላ በዐጹ ዘድንግል ዘመነ መንግሥት በ ዓም በአባ ጴጥሮስ ፖኤዝ የሚመሩ ላቲኖች ወደ ሀገራችን ገቡ የፖርቹጋል መንግሥት ባደረገው ውለታ ምክንያት በሀገራችን እንዲቀመጡ ስለተፈቀደላቸው በሀገራችን ተቀምጠው በተለያዩ አጋጣሚዎች ሁሉ እምነታቸውን በድብቅ ማስፋፋት ጀመሩ በዚህ መልኩ ከቀጠሉ በኋላ በይፋ ደረታቸውን ነፍተው ልባቸውን ሞልተው በኩራት እምነታቸውን ማስፋፋት የጀመሩት ግን በዐጹ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት ነበር ፈሊጥ አዋቂው ጴጥሮስ ፖኤዝ የሀገራችንን ቋንቋ ግእዝን ተምሮ ይሰብክ እና ይቀድስ እንደነበር ይነገራል ከንጉው ዘንድም እየሄደ የካቶሊክ እምነትን ቢቀበሉ የፖርቹጋል መንግሥት የጦር መሣሪያን ያስታጥቅዎታል እያለ ይሰብካቸው ነበር ንጉውም በዚህ ተታልለው ለካቶሊኮች የቤተክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ሰጧቸው በኋላም በ ዓም በጴጥሮስ ፓኤዝ እጅ ከነቤተሰቦቻቸው በሮማ ካቶሊክ ሥርዓት ተጠምቀው ካቶሊክነታቸውን በይፋ አረጋገጡ የጴጥሮስ ፓኤዝን ሞት ተከትሎ በሮማው ጳጳስ እጅ ጵጵስና የተሾመው የእስፔኑ ተወላጅ አልፎንሱ ሜንዴዝ በየካቲት ዓም የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ተብሎ ተሰይሞ ወደ ሀገራችን ሰኔ ቀን ዓም ገባ ከዚህ የካቶሊክ ፓትርያርክ ጋር አንድ ረዳት ኤዲስ ቆጾስ እና ቀሳውስት አብረውት ተልከው ወደ ሀገራችን ገብተዋል ንጉሥ ሱስንዮስ የካቲት ቀን ዓም የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ካቶሊክ እንዲሆን እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሮም ሥር እንድትተዳደር ዐዋጅ ዐወጁ ከዚህ በኋላ ንጉውሁ ከአልፎንሱ ሜንዴዝ ጋር ተባብረው የሚከተሉትን ህጎች አወጡ ወ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እንደገና እንዲጠመቁ ወ ካህናቱም እንደገና እንዲካኑ ወ አብያተ ክርስቲያናትም እንደገና በሮማውያን እንዲባረኩ ወ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ቅዱሳት ሥዕላት ቀርተው በሮማውያን ሥርዓት የተቀረጹ ምስሎች እንዲቆሙ ወ የሮማውያን የቀን መቁጠሪያ በኢትዮጵያ እንዲሠራበት ወ የአርብና የረቡዕ መጾም ቀርቶ ቅዳሜ እንዲጾምና የቅዳሜ ሰንበትነት እንዲሻር ይህንን ህግ የማይጠብቅ ሁሉ የአካል ቅጣት እንደሚወሰድበት ንጉሠ ዐዋጅ እንዲያውጁ አልፎንሱ ሜንዴዝ ስለነገራቸው ንጉሁም በዚሁ ተስማምተው ዐዋጁን ዐውጀዋል በዚህም የተነሣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጳጳስ የሆኑት አቡነ ስምኦን ለሃይማኖታቸው ተቆርቋሪ የሆኑትን ካህናት መኳንንት እና ምእመናን ሰብስበው ከንጉሠ ጋር ጦርነት ከፈቱ የንጉሁን ተከታዮች ለመቀነስም አቡነ ስምኦን ንጉው የአባቶቻችንን ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለውጠዋልና እርሳቸውን የሚከተል እንደ አርዮስ የተወገዘ ይሁንን ብለው የንጉሁን ተከታዮች በማውገዝ ድጋፋቸውን አጠናከሩ ሆኖም ግን ድሉ ለንጉሠ ሆነና ጳጳሱም በዚሁ ጦርነት ተገደሉ በዚህም የተነሣ በካቶሊካውያኑ ዘንድ ንዴትን ፈጠረ እና የተዋሕዶ እምነትን በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ ስቃይ አጸኑባቸው ይህንን በክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና መከራ የሰሙ የጎጃም ቤጌ ምድር የትግራይና የላስታ ሰዎች ሰማእትነት እንዳያመልጠን እያሉ ወደ ሱስንዮስ ዐደባባይ ስለመጡ ብዙ ክርስቲያኖች ተገድለዋል ይህ ጦርነትም ለሰባት ዓመታት ያህል ከተካሄደ በኋላ ንጉው ታመሙና አንደበታቸው ተዘጋ ልጃቸው ፋሲልም ወደ ገዳማትና አድባራት በመሄድ አባቴ የክርስቲያኖችን ደም በማፍሰሱ እግዚአብሔር ተቆጥቶበት አንደበቱ ተዘግቷልና ጸልዩለት የምትፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ አለ በዚህ የፋሲል ልመና የማኅበረ ሥላሴው አምደ ሥላሴ የተባሉ ባሕታዊ የገዳማቸውን መነኮሳት አስከትለው በመሄድ ለሦስት ሱባኤ ያህል በጸሎት በምህላ ቆይተው ጸበል አጠመቋቸው ንጉውም አንደበታቸው ተከፈተ መናገር ቻሉ በዚህ ጊዜ ለልጃቸው «የእስክንድርያ ሃይማኖት ትመለስ የሮም ሃይማኖት ትርከስ ፋሲል ይንገሥ ብለህ ዐዋጅ ተናገርን ብለው ነገሩት እርሱም ዐዋጁን ዐወጀ ህዝቡም ተደሰተ አድባራትና ገዳማትም የደስታ ደወላቸውን ደወሉ በአልፎንሱ ምክንያት የተሰደዱት በየዋሻው በየበረሃው የገቡ መምህራን መነኮሳት ሁሉ መጽሐፎቻቸውን እና ጽላቶችን እየያዙ ወደየቦታቸው ተመለሱ በካቶሊካውያኑ ተታልለው ሃይማኖታቸውን የለወጡትንም ንስሐ እንዲገቡ እያደረጉ ወደ ቤተክርስቲያን መለሷቸው ከዚህ በኋላ ንጉሁ ሞቱና ልጃቸው ፋሲል ነገሠ ህዝቡ ይበልጥ ደስ አለው አልፎንሱ ግን እስካሁን ድረስ ከሀገራችን አልወጣም ነበር ዐጹ ፋሲል መንግሥቱን ካደላደለ በኋላ የተዋሕዶ ሊቃውንት ከአልፎንሱ ሜንዴዝ ጋር በጎንደር ጉባኤ ተደርጎ ተከራከሩ በዚህም ጉባኤ በዕጨጌ በትረ ጊዮርጊስ መሪነት የተከራከሩት የተዋሕዶ ሊቃውንት አሸነፉ የመጀመሪያ ጠያቂው አልፎንሱ ሜንዴዝ «አብ የባሕርይ ልጁ ሞተ የሚለው ገጸ ንባብ ከምን ይገኛል» ብሎ ጠየቀ። ጥያቄ አንተ በራስህ አንቅተህ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ቃል ሥጋ በኾነ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረበት መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የጸጋ ልጅ ኾነ እያልህ ታስተምራለን። የዛሬዎችም በመጽሐፋቸው «ወልደ አብ ገጽ » አጣ ደሐየ ተቸገረ ዜገን ሲሉ «ይህ የጸጋ ልጅነት የሌለው ባእድ ሥጋ እምቅድመ ዓለም የባሕርይ ልጅነት ካለው መለኮት ጋራ ቢዋሐድ የቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነት አገኘ ይህ ልጅነት ያለው ቃል ልጅነት ከሌለው ሥጋ ጋራ ቢዋሐድ በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ኾነ» ብለዋል ቀጥለውም ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን ሲገልጹ ወልደ አብ ገጽ ላይ « መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ ቢወለድ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክ የባሕርይ ልጅ ኾነ» በማለት ጽፈዋል። በተጨማሪም ወልደ አብ ገጽ ላይ ፈወልድስ በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ባይወለድ ወልድ በሰውነቱ እንደ አብ ባልገዛም አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን በመላ በሰፋ ባልሰጠውም ነበር» በማለት አብን ሰጭ ወልድን ደግሞ ተቀባይ መንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሲያደርጉ ይታያሉ ስለዚህ ነው እንግዲህ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስን ጠቀመው ረባው ማለታቸው መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ባይወለድ ኖሮ ወልድ እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ መግዛት ማዘዝ አይችልም ነበር ማለታቸው ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገዋል ማለታቸው ነውና ከመጀመሪያዎቹ የቅባት ክፍል ጋር አንድነት አላቸው ወልደ አብ ገጽ ቋ ላይ ደግሞ ለመለኮት የማይቀፀል ቃል እንዲህ ብለው ቀፀሉ «በዚህም በባሕርይ ልጅነቱ እኛ ብቻ ተጠቅመንበት አልቀረንም እርሱም ተጠቀመበት እንጂ» ይላሉ። የዛሬዎቹም ወልደ አብ ገጽ ቋ ላይ ፈተዋሕዶ ክብር የሚያሳልፍ ንዴትን የሚያጠፋ መስሏቸው የቃልን ክብር ለሥጋ ካሳለፍን ብለው ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ ቢያጡለት በተዋሕዶ ከበረ ቅብዐት አልረባውም ብለው ጂ ተነሥተዋል ለሊህ ምን ይመልሷል ቢሉ ተዋሕዶማ ኹለትነትን አጠፋ አንድነትን አጸና እንጂ ንዴትን አላጠፋም ክብርን አላሳለፈም» ይላሉ ተዋሕዶ ለእነርሱ ኹለትነትን አጥፍቶ አንድነትን ብቻ ያጸና ነው እንጂ የሥጋ ንድየት በቃል ባዕልነት እንዳልተወገደ ነው የሚያምኑት እኛ ደግሞ ኹለትነት ጠፍቶ አንድነት ሲጸና የሥጋ ንድየት በቃል ባዕልነት ተወግዶ ቅድምና የሌለው ሥጋ ቀዳማዊ አምላክ ኾነ እንላለን ሰው አምላክ ኾነ አምላክ ሰው ኾነ ማለት ስለዚህ ነው የሥጋ ገንዘብ ከኃጢአት በቀር ለመለኮት የመለኮትም ገንዘብ ለሥጋ ገንዘቡ ኾነ የምንለው በተዋሕዶተ መለኮት ነው እንጂ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ሦስተኛው ባህላቸው በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን የተነሠት እነአለቃ ጎሹ በቅብዐት ብቻ ማለትን ነቅፈው ፈመጽሐፍ በኹለቱም ኹሉ በተዋሕዶ ከበረ በቅብዐት ከበረ ይላልና ቅብዐት ያለተዋሕዶ ተዋሕዶም ያለቅብዐት ብቻ ብቻውን አያከብርም በተዋሕዶና በቅብዐት በአንድነት የአምላክነት ክብር ከብሮ የባሕርይ ልጅ ኾነ» ብለዋል። በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ይላሉ። ልዩነታችን ቅብዐቶች የጌታ ልደት በዓል ኹል ጊዜ ታኅሣሥ ቀን መከበር አለበት ይላሉ። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት ክፍል የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት ቅብዐቶች ወልድን ፍጡር ይሉታል እኛ ግን ፈጣሪ ነው እንለዋለን። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት ቅብዐቶች ለቅዱሳን እና ለመስቀል ስግደት አይገባም ይላሉ እኛ ግን ይገባል እንላለን። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት ክፍል የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት ቅብዐቶች ወንጌል በአሚን ብቻ ታድናለች ይላሉ እኛ ግን አሚን ያለምግባር ብቻውን አያድንም እንላለን። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት እነርሱ «በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ» እኛ ደግሞ «ፈበተዋሕዶ ከበረ» እንላለን። እኛ የተዋሕዶ ልጆች በተዋሕዶተ ቃል ሥጋ ክቡር አምላክ ሆኗልና በተዋሕዶ ከበረ እንላለን ይህንንም ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ ድርሳን ቁጥር ላይ እንዲህ ይላል «አብን በልብነት መንፈስ ቅዱስን በእስትንፋስነት ገንዘብ ለማድረግ ሥጋ ቃልን ተዋሐደ» ስለዚህ ሥጋ የአብን ልብነት የመንፈስ ቅዱስን እስትንፋስነት ገንዘቡ ያደረገው ቃል ስለተዋሐደው እንጅ መንፈስ ቅዱስ በቅብዐትነት ስላከበረው አይደለም ማለት ስለዚህ ነው ቅዱስ ቄርሎስ በሃይማኖተ አበው ስምዐት ላይ ፈወካዕበ ይቤ እስመ ክርስቶስ ኢተቀብዐ በእንተ መፍቅድ ዘቦቱ አላ ለሊሁ ቀባዒ ውእቱ ወዐርገ ኀበ ሥልጣነ መለኮቱ እንዘ ሰብእ ውእቱ ወለሊሁ እግዚአብሔር አምላክ ተብህለ በእንቲአሁ ከመ ውእቱ ተለዐለ ፈድፋደ በእንተ ትህትና ወሕጸጽ እንተ ዘትስብእት ወንዴት ወለሊሁ ጸገዎ ስመ ዘላዕለ ኩሉ ዝንቱ ዘኮነ በህላዌ ከመ አምላክ ከመ ያልዕለነ ለነሂ ዓዲ ኀበ ሀሎ ዝኩ ዳግመኛ ክርስቶስስ ክብር መሻት ኖሮበት አልከበረም እርሱ ራሱ አክባሪ ነው እንጅ ሰው ቢኾንም በባህርይ ክብሩ ከበረ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር አምላክ ነው ሥጋ ትሁት ሕጹጽ ነዳይ ስለሆነ ተለዐለ ተብሎ ተነገረለት ከሁሉ በላይ የሆነ ስምንም እሱ ራሱ ሰጠው ተባለ ይህም የሆነ በባህርይ ተዋሕዶ ነው አምላክ እንደሆነ እኛንም እሱ ወደ አለበት ያቀርበን ዘንድ» ይላል። በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ» የሚለው አነጋገር ግን ከዚህ የተለየ ነው። አካላዊ ቃል ፈጥሮ የተዋሐደውን ሥጋ ማክበር የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ይላሉ። መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ የሚሉትን የጸጋ ልጆችንና ቅብዐቶችን ግን ገዘቱ» መድሎተ አሚን ገጽ ላይ ፈየኢትዮጵያ ሃይማኖት በሕግ ተወስኖ ጳጳሳቱ ክህነት የሚሰጡበት ንጉሠ ተቀብቶ የሚነግሥበት ሕዝቡ ተስማምቶ የሚኖርበት ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኹለት ልደት በተዋሕዶ ከበረ ማለት እንደኾነ በሕገ መንግሥት ተጽፎ አንዱን ክፍል አንቀጽ ይዞ ይገኛልን መድሎተ አሚን ገጽ ላይ ፈወልድ ቅብዕ ማለትና መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ማለት በተዋሕዶ የባሕርይ አምላክ ኾነ ማለትና በቅብዐት የባሕርይ ልጅ ኾነ ማለት መገናኘት የማይቻላቸው ልዩ ልዩ ነገሮች መኾናቸውን ሊረዱ አልቻሉም» መድሎተ አሚን ገጽ ላይ ፈእንዲያውም በጠቅላላው ዛሬ በኢትዮጵያ ኹሉም ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኹለት ልደት በተዋሕዶ ከበረ የሚል ነው እንጂ ከዚህ ወጥቶ አንድ አካል ኹለት ባሕርይ በቅብዐት የጸጋ ልጅ በቅብዐት የባሕርይ ልጅ የሚል አይገኝም» በአጠቃላይ «አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ብሎ ማመን የሚከተሉትን ስህተቶች ያመጣል። ኛ የአካላት ግብር ስም ኹለት ጊዜ እንደተሰጣቸው ያሳያል ዘመን ሳይቆጠር ቀድሞ «አብ ቀባዒ ወልድ ቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቀባዒ» ድኅረ ዓለም ወልድ በሥጋ ማርያም በተገለጠ ጊዜ ደግሞ «አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ» ሆኑ ማለት ነው ይህ ደግሞ የግብር መቀዳደምን እና መለዋወጥን ያሳያል ኛ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ ምእራፍ ቁጥር ላይ «ለአጽንዖተ ክልዔሆሙ አብን መንፈስ ቅዱስን በጥንተ ስማቸው ለማስጠራት በጥንተ ግብራቸው ለማጽናት» የሚለው ትምህርት ተቀባይነትን አላገኘም ማለት ነው ኛ አብ ከቀባዒነት ወደ ቀባዒነት ወልድ ከቀባዒነት ወደ ተቀባዒነት መንፈስ ቅዱስ ከቀባዒነት ወደ ቅብዕነት እንደተለወጡ የሚያሳይ መሆኑ ይህ ደግሞ ወልድን ክብር አልባ ነው ያሰኛል። እዚህ ጽሑፍ ላይ በዋናነት ሦስት መሠረታዊ ስህተቶችን እንመለከታለን ኛ በመጻሕፍት ተጽፎ የማናገኘው «አብ ወልድን በማኅጸነ ማርያም በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ወለደው» የሚል ስህተት አለበት ኛ መጻሕፍት «ፈለሰማያዊ ልደቱ እናት ለምድራዊ ልደቱም አባት አትሹለት» እያሉ እዚህ ላይ ግን ፈለምድራዊ ልደቱ አባት ሽተውለታል» ስለዚህም ኹለተኛ ስህተት ብለን ቆጠርነው ኛ የተቀመጠው ምሳሌ «ሦስት ጊዜ የተቆጠረውን ልደት ኹለት» ብለን እንድንቀበለው የሚያደርግ ማስረጃ አለመሆኑ በእነዚህ ቅደም ተከተሎች በማስረጃ እያስደገፍን የዚህን ስህተት እናጋልጣለን ፈወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ» የምንል ክርስቲያኖች የምናምናቸው ልደታት ኹለት ናቸው እነዚህም ኛ ቅድመዓለም ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል ሳይቀድም ሳይከተል በዚህን ጊዜ ተወለደ በማይባል ረቂቅ ጥበብ ወልድ ከአብ ያለ እናት የተወለደው ቀዳማዊው ልደት ነው ኛ የአዳምን በደል ለማጥፋት ከሴት የሚወለድበት ዘመን በደረሰ ጊዜ በኅቱም ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ በተዋሕዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት የተወለደው ደኃራዊው ልደት ነው ሊቃውንቱ ፉቀዳማዊ ልደቱ በደኃራዊ ልደቱ ታወቀ» ይላሉ ሁለቱም ልደታት ከሰው ኅሊና በላይ ከመመርመርም እጅግ የራቁ ናቸው ማንም እነዚህን ልደታት መርምሮ አይደርስባቸውም በረቂቅ ምሥጢር የተከናወኑ ናቸውና ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን የምትቀበላቸው የምታምናቸው የምታስተምራቸው በመጻሕፍት የጻፈቻቸው የጌታ ልደቶች ቅድመ ዓለም ያለእናት ከአብ በመለኮት የተወለደው ልደት እና ድኅረ ዓለም ያለአባት ከቅድስት ድንግል ማርያም መለኮት በሥጋ የተወለደው ልደት ነው ከዚህ ውጭ በቅብዐቶች ዘንድ «ወልድ በማኅጸነ ማርያም በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ተወልዷል» የሚለው ሦስተኛው ልደት በየትኛውም የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት ዘንድ ተመዝግቦ አናገኘውም ለዚህም በርካታ ማስረጃዎችን ማሳየት ይቻላል። ይህ ፈሦስተኛው ልደት» ከየት መጣ ስንል አንድ የሚጠቅሱት ጥቅስ አለ እርሱም መጽሐፈ ምሥጢር ምእራፍ ቁጥር ጃጃ ነው ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዚህ መጽሐፉ ላይ የጻፈው እንዲህ የሚል ነው ፈነገርነኬ በእንተ ህላዌ መለኮቱ ወትስብእቱ እምድኅረ ስጋዌሁ ኢንቤሎ ወልደ እግዚአብሔር በመለኮቱ ወወልደ እጓለእመሕያው በትስብእቱ ድንግልኒ ወለደት ዘኢዚአሃ መለኮተ በዘዚአሃ ሥጋ ምስለ ዘዚአሃ ሥጋዌ አብኒ ወለደ ዘዚአሁ ሥጋ በዘዚአሁ መለኮት ምስለ ዘዚአሁ ኃይል ዘህሉና አምላክ ስለመለኮቱ እና ስለ ትስብእት ህልውና እነሆ ተናገርን ሰው ከመሆኑ በኋላ በመለኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ በሰውነቱም የሰው ልጅ አንለውም ድንግልም ለእርሷ በተገባ ሥጋዌ የእርሷ በኾነ ሥጋ የእርሷ ያልኾነውን መለኮት ወለደችው አብም የባሕርይው ያልኾነውን ሥጋ የባሕርዩ ከኾነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የእርሱ በኾነ መለኮት ወለደ» የሚል ነው ከዚህ ትምህርት መካከል ቅብዓቶች አብ በማኅጸነ ማርያም ወልዶታል ለሚለው ክህደታቸው ቆርጠው የወሰዱት «አብም የባሕርይው ያልኾነውን ሥጋ የባሕርዩ ከኾነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የእርሱ በኾነ መለኮት ወለደ» የሚለውን ነው ሊቁ ወደ ምሥጢር ሄዶ ፈአብም የባሕርይው ያልኾነውን ሥጋ የባሕርዩ ከኾነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የእርሱ በኾነ መለኮት ወለደ» ብሎ ተናገረ ከተዋሕዶ በኋላ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብም ለቃል ገንዘቡ እንደኾነ እናምናለን ስለዚህ ቃል ከሥጋ ጋራ በተዋሐደ ጊዜ ሥጋ ፈወልደ አብ ቃለ አብ» መባልን ገንዘቡ አደረገ ማለት ነው ሥጋ ቀዳማዊ አምላክ ኾነ ቀዳማዊ አምላክ በመሆኑም ወልደ አብ ተባለ ማለትም ሥጋ የአብ ልጅ ተባለ ማለት ነው ለወልድ አባቱ የኾነ አብ ለክርስቶስም ለሥግው ቃልን አባቱ ተባለ ማለት እኮ ነው ቃል ከአብ በመለኮት የተወለደበት ልደት ለሥጋም ገንዘቡ ኾነ ሲል ነው። ስለዚህ ሥጋ ወልደ አብነትን የአብ ልጅ መባልንን ገንዘቡ አደረገ አለ ሊቁ ይህን ምሥጢር አርቀቆ የተናገረበት ግሩም ትምህርት እንደኾነ በዚህ እንረዳለን ቅብዐቶች ከላይ እንደጻፍነው ፈእምቅድመዓለም በመለኮቱ ተወለደ ብለናል ኋላም በማኅጸን በሰውነቱ ከአብ ተወለደ እንላለን ዳግም ከእመቤታችን በስጋ በጎል ተወለደ እንላለን ይህማ ሦስት አይደለምን እንደምን ኹለት ነው ቢሉ እምቅድመዓለም በመለኮቱ የተወለደው ልደትና ዛሬ በማኅጸን በሥጋ በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ የተወለደው ልደት አንድ ልደት ይባላል እንጅ ኹለት አይባልም። እዚህ ላይ በግልጥ የምንመለከተው ሦስት ልደታትን ማመናቸውን ነው መጻሕፍት «ኹለት ልደታትን እናምናለን» ብለው ስላጠሩባቸው ለመንፈራገጥ አልመች ቢላቸው ሦስት ጊዜ ቆጥሮ ኹለት ማለት ይገባል ብለው ተናገሩ እነርሱ የሚጠቅሷቸው በግልጥ የተቀመጡት የጌታ ልደቶች እነዚህ ናቸው ኛ እምቅድመ ዓለም በመለኮቱ የተወለደው ልደት ኛ በማኅጸን በሥጋ በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ የተወለደው ልደት ኛ ከእመቤታችን በስጋ በጎል ተወለደ በማለት ሦስት ልደታትን አስቀምጠውልናል ከእነዚህ ልደታት መካከል ኛው ልደት በየትኛውም መጽሐፍ ተጽፎ እንደማይገኝ ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች በማስረጃ በማስደገፍ ጽፈናል እነርሱ እንደሚሉት ኛ እና ኛ ላይ የተገለጡት ልደቶች አንድ ተብለው ይቆጠራሉ እንጅ ኹለት አይባሉም ይላሉ ለምን ለሚለው መልስ ሲመልሱ «ኹለት ጊዜ ቆጥረነው አንድ ማለታችን እንዴት ነው ቢሉ እምቅድመዓለም በመለኮቱ የወለደው አብ ነው። እዚች ላይ ያዝ አድርጓት እስኪ የቀደመ ልደቱ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ሳይቀድም ሳይከተል ያለእናት በመለኮት በረቂቅ ምሥጢር የተደረገ ነው የዛሬው ልደቱ ደግሞ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ በመለኮት አይደለም ምክንያቱም አብ የወለደው በሥጋ ነው ብለውናላ በመለኮት ነው ካሉ ወልድ በመለኮቱ ስንት ጊዜ ተወለደ ብለን እንጠይቃቸዋለን በሥጋ ነው የወለደው ካሉን ደግሞ መለኮታዊ አካል ሥጋዊ አካልን መለኮታዊ ባሕርይም ሥጋዊ ባሕርይን ይወልድ ዘንድ ይቻላልን ብለን እንጠይቃቸዋለን አዎን ሊወልድ ይቻለዋል ካሉን የቀደመው ልደቱ ከአብ በመለኮት ነው የዛሬው ልደቱ ደግሞ ከአብ በሥጋ ነውና ኹለት ብለን እንቆጥረዋለን እንጅ አንድ ልደት አንለውም ብለን በዚህ እንረታቸዋለን ነገር ግን እነርሱ መረታትን ስለማይሹ «ፉወላዲው ተወላዲው ዛሬም የተወለደበት መንፈስ ቅዱስ ያ የጥንት የባሕርይ ሕይወቱ ስለአልተለወጠ አንድ ልደት ይባላል እንጅ ኹለት ልደት አይባልም» ብለው መከራከራቸው አይቀርም ነገር ግን ወላዲው አብ ይኹን ተወላዲውም ወልድ ይኹን አይቀየር አይለወጥ እንጅ ልደቱ ግን ለየቅል ነው እንላቸዋለን ምክንያቱም ፈየቀደመው ልደት በመለኮት የዛሬው ልደት በሥጋ» ነውና ልደቱ በጣም ይለያያል እንላቸዋለን አብ በመለኮት ቅድመ ዓለም የወለደው ልደት እና ዛሬ በማኅጸነ ማርያም በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ወለደው የሚሉት ልደት እጅግ የተለያየ እንደኾነ ልብ ማለት ተስኗቸዋል ለዚህም እኮ ነው ይች «ዛሬ አብ በማኅጸነ ማርያም በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ወለደው» የምትለዋ ተጨማሪ የፍልስፍና ልደት ትቅር መጽሐፍ አይደግፋትም የምንለው የጻፉትን ነገር ስትመለከቱት ፈራሽ ነገር ነው ቀጥለው ለዚህም ምሳሌ ያስረዳል ይሉናል ልብ በሉ። ወልደ አብ ገጽ ላይ ፈበቅብዐት የባሕርይ ልጅ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው ምነው ይህስ ቢኾን ወልድ በአብ ያልተወለደ በራሱ ያልተወለደ ስለምን በመንፈስ ቅዱስ ተወለደ ቢሉ ይህስ ወላዲ በሚመስለው ሕይወት ይወልዳል እንጅ በማይመስለው አይወልድም ለዚህም ምሳሌ ያስረዳል እነሆ ዛሬ በደመ ነፍስ ሕያዋን የሆኑ እንስሳ ከእንስሳ ይወለዳሉ በነባቢትም ነፍስ ሕያው የኾነ ሰው ከሰው ይወለዳል መንፈስ ቅዱስ ለአብ ሕይወቱ ነው በደመ ነፍስ ሕያው ያልኾነ ከእንስሳ በነባቢት ነፍስ ሕያው ያልኾነ ከሰው እንዳይወለድ እንደዚህም ኹሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ያልኾነ ከአብ አይወለድምና ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከአብ ተወለደ» ይላል እስኪ ቃል በቃል እንመልከተው ወ በቅብዐት የባሕርይ ልጅ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው ኹላችን እንደምናውቀው በከዊን አብን «ልብ» ወልድን «ፈቃል» መንፈስ ቅዱስን «እስትንፋስ» እንላለን የአብ ፈልብነት» ከወልድ «ቃልነት» ከመንፈስ ቅዱስም «ሕይወትነት ርስትንፋስነትን» አይቀድምም አይከተልምም በተመሳሳይ የወልድ «ቃልነት» ከአብ «ልብነት» እና ከመንፈስ ቅዱስ «እስትንፋስነት» አይይቀድምም አይከተልምም የመንፈስ ቅዱስም «ሕይወትነት ሁስትንፋስነትን» ከአብ «ልብነት» ከወልድ «ቃልነት» አይቀድምም አይከተልምም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ለአብ እና ለወልድ እስትንፋሳቸው ነው ማለት የባሕርይ ሕይወታቸው ነው ማለት ነው በቅብዐት እምነት ውስጥ ግን «ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ» ይላሉ እንግዲህ ፈወልድ» ማለት ልጅ ማለት እንደኾነ እናውቃለን ልጅነቱም ከአብ የባሕርይ ልጅነት ነው ይህ ፈወልድ» የሚለው ስም አብ «አብ» ከተባለበት መንፈስ ቅዱስም «መንፈስ ቅዱስ» ከተባለበት ጥንት ከሌለው ዘመን ስሙ አይቀድምም አይከተልምም ስለዚህ ፈወልድ» የሚለው ስም የተገባው የኾነ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ አይደለም ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜስ «አማኑኤል» «ኢየሱስ» «ክርስቶስ» ተባለ እንጅ ወልድ የተባለውስ ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ «ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል» ከአብ በተወለደ ጊዜ ነው ስለዚህ ይህ «ወልድ» የመንፈስ ቅዱስን ሕይወትነት ያገኘው ገንዘቡ ያደረገውን ዛሬ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ ሳይኾን ጥንት ከአብ ተወልዶ ፈወልድ»ን ተብሎ በተጠራበት ጥንት በሌለው ጊዜ ነው ስለዚህ «ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ» ቢባል ክህደት ነው አንጅ እምነት አይባልም ምክንያቱም «ፈአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነውና ወልድም በአብና በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነውና መንፈስ ቅዱስም በአብና በወልድ ህልው ነውና» እንዳሉ የቀደሙ አባቶቻችን በሃይማኖተ አበው ዘዲዮናስዮስ ሩ ላይ። ስለዚህ ይህ ህልውና ቀድሞ ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ ያለ በመሆኑ እና ወልድ ከዚህ ህልውናው የተለየበት ጊዜ ስለሌለ «ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ» ቢባል ክህደት ነው ፈበቅብዐት የባሕርይ ልጅ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው» ማለትን ከማን እንደተማሩት አይታወቅም አብ በመለኮቱ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ወለደው እንጅ ድኅረ ዓለምም ዳግመኛ በሰውነቱ ከእናት አልወለደውም በሰውነቱስ ከአብ ዳግመኛ ተወልዶ ቢኾን ኖሮ «ወልደ አብ» መባል «ወልደ ማርያም» ከመባል በበለጠበት ነበር ነገር ግን ቅድመ ዓለም ፈኗወልደ አብ» የተባለው ድኅረ ዓለም «ፉወልደ ማርያም» ቢባል እኩል ነው አንጅ አይበላለጥም እንዲያውም ሊቃውንቱ ሲያመሰጥሩ «ፈቀዳማዊ ልደቱ በደኃራዊ ልደቱ ታወቀ» ይላሉ ይህ ማለት «ፉወልደ አብ» መባሉ ፉወልደ ማርያም» በመባሉ ታወቀ ተገለጠ ማለት ነው ሃይማኖተ አበው ዘቴዎዶጦስ ሂደ ላይ ፈወልድ ዋሕድ ከአብ መወለዱ እንዴት እንደኾነ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱ እንዴት እንደኾነ አትጠይቀኝ እርሱ በባሕርዩ ከአብ ተወልዷልና ለራሱ በአደረገው ተዋሕዶም ከድንግል ማርያም ተወልዷልና አምላክ ነው ሰውም ነው» ይላል ሊቁ «ለራሱ በአደረገው ተዋሕዶም ከድንግል ማርያም ተወልዷልና አምላክ ነው ሰውም ነው»ን አለ እንጂ ፈወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው» አላለም ሊቃውንቱ «ትስብእት የመንፈስ ቅዱስን ሕይወትነት ገንዘቡ አደረገ» ይላሉ። ፉምነው ይህስ ቢኾን ወልድ በአብ ያልተወለደ በራሱ ያልተወለደ ስለምን በመንፈስ ቅዱስ ተወለደ ቢሉ ይህስ ወላዲ በሚመስለው ሕይወት ይወልዳል እንጅ በማይመስለው አይወልድም» ይኹኛው ከመጀመሪያ ሐሳባቸው ጋር ይጋጫል ምክንያቱም ቅድም «ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው» ብለው ነበር አሁን ግን ፈምነው ይህስ ቢኾን ወልድ በአብ ያልተወለደ» በማለት ሐሳባቸውን ራሳቸው ያጣሉታል በእርግጥ መጽሐፋቸው ሙሉውን እንደዚህ እርስ በእርሱ የተጣረሰ ሐሳብ የሰፈረበት ነውና አይገርምም እሽ ይኹን ብለን ብንቀበለው እንኳ ፈወላዲ በሚመስለው ሕይወት ይወልዳል እንጅ በማይመስለው አይወልድም» ስላሉ መንፈስ ቅዱስን «ፈወላዲን ያሰኛልና አንቀበለውም አብን ፈወላዲ» «አሥራጺ» ወልድን ፈተወላዲጋ መንፈስ ቅዱስን «ሠራጺ» ብንል እንጅ መንፈስ ቅዱስን «ፈወላዲን እንዳንል እነሆ የታወቀ የተረዳ ነው «ወላዲ በሚመስለው ሕይወት ይወልዳል» አልን እንጅ መቼ «ወላዲ» ነው አልን ቢሉም ወላጅ የሚመስል ሕይወት የለም ብለን እንመልሳለን ወ «ለዚህም ምሳሌ ያስረዳል እነሆ ዛሬ በደመ ነፍስ ሕያዋን የሆኑ እንስሳ ከእንስሳ ይወለዳሉ በነባቢትም ነፍስ ሕያው የኾነ ሰው ከሰው ይወለዳል መንፈስ ቅዱስ ለአብ ሕይወቱ ነው በደመ ነፍስ ሕያው ያልኾነ ከእንስሳ በነባቢት ነፍስ ሕያው ያልኾነ ከሰው እንዳይወለድ እንደዚህም ኹሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ያልኾነ ከአብ አይወለድምና ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከአብ ተወለደ» በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ረቂቅ ልደት በእንስሳት እና በሰው ልጅ ልደት ልንመስለው እንዴት እንችላለን። ሰው ቢወለድ ከእናት እና ከአባቱ ዘር ነው እንጅ በድንግልና አይደለም እንስሳትም ከእንስሳት ቢወለዱ እንዲሁ በተራክቦ ነው እንጅ በድንግልና አይደለም የወልድስ ከድንግል ማርያም መወለድ በማክሰኞ ቀን ኅቱም ምድር ለታብቁል ባለው ቃል አብቅላ አፍርታ እንደተገኘች ያለ ነው ሰው ከሰው የተለየ እንስሳን እንስሳም ከእንስሳ የተለየ ሰውን ይወልዱ ዘንድ ፈጣሪ ተአምሩን ከገለጸ ይወልዳሉ ይህንንም በተለያዩ ዜናዎች እየሰማን እና እየተመለከትን ነው ስለዚህ ይህ ምሳሌ «ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው» ለሚለው ማስረጃ ሊኾን አይችልም ፈእንደዚህም ኹሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ያልኾነ ከአብ አይወለድምና ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከአብ ተወለደ» ብለው ክህደታቸውን በአራት ነጥብ ይቆልፉታልበመንፈስ ቅዱስ ሕያው ያልኾነ ከአብ ካልተወለደ በቀዳማዊ ልደቱ አብ ወልድን የወለደው የባሕርይ ሕይወቱ ከኾነው መንፈስ ቅዱስ ሕያው ከኾነ በኋላ ነውን ቢሏቸው መልስ የላቸውም በነገራችን ላይ ፈበግብረ መንፈስ ቅዱስ» የሚለውን የሊቃውንቱን ትምህርት በማጣመም ነው ለራሳቸው እየተጠቀሙበት ያሉ። ወልደ አብ ገጽ ላይ «ይህ የጸጋ ልጅነት የሌለው ባእድ ሥጋ እምቅድመ ዓለም የባሕርይ ልጅነት ካለው መለኮት ጋራ ቢዋሐድ የቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደአብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነት አገኘ ይህ ልጅነት ያለው ቃል ልጅነት ከሌለው ሥጋ ጋራ ቢዋሐድ በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ኾነ እንዘ ባዕል ውእቱ በኩሉ አንደየ ርእሶ እን ጳውሎስ ኛ ቆሮ ም ቁ ስለዚህ ከእምቅድመ ዓለም ልደቱ ድ ለማድረግ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱን በመላ ተቀብሎ ከአብ ተወለደ እንጅ የቀደመ ልጅነቱስ አልተነሣውም ወልድስ በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ባይወለድ ወልድ በሰውነቱ እንደ አብ ባልገዛም አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን በመላ በሰፋ ባልሰጠውም ነበር ኢይሁብ ክብርየ ለባዕድ ለተሳትፎ ወስብሐትየ ለግልፎ እን ኢሳ ምሟ ቁ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ቢወለድ ግን እንደአብ ገዛ አዘዘ አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን ሰጠው። እስኪ አሁንም ቃል በቃል እንመልከት ፈይህ የጸጋ ልጅነት የሌለው ባእድ ሥጋ እምቅድመ ዓለም የባሕርይ ልጅነት ካለው መለኮት ጋራ ቢዋሐድ የቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነት አገኘ» ሥጋ ከፈጣሪው የጸጋ ልጅነትም የለውም ነበር ማለታቸው አዳም ስለበደለ እና ጸጋ እግዚአብሔር ስለተገፈፈበት ነው ኾኖም ግን እምቅድመዓለም የባሕርይ ልጅነት ያለው መለኮት ሲዋሐደው የቃልን ገንዘብ ገንዘቡ አደረገ እና ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነትንም አገኘ ብለው ይደመድማሉ በጣም ጥሩ ነው አሁን ላይ መለኮት ሲዋሐደው ሥጋ አምላክ ኾነ ክቡር ኾነ የቃል ገንዘብ ገንዘቡ ኾነ እና ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ማለት ነው ይህ ነው በተዋሕዶ ከበረ ማለት። ነገር ግን ቀጥለው ይህንን ያፈርሱትና «ይህ ልጅነት ያለው ቃል ልጅነት ከሌለው ሥጋ ጋራ ቢዋሐድ በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ኾነ» ከላይ ፉየቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደአብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነት አገኘ» ብለው ነበር አሁን ደግሞ እንደገና ተመልሰው «በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ኾነ» ብለው የሚጋጭ ሐሳብ አስፍረዋል ለዚህ ሐሳባቸውም የሚደግፍ ማስረጃ ብለው ሰውን ለማደናገር ግዕዙን ብቻ ጠቅሰው አማርኛውን ሳያስቀምጡት አለፉ አብዛኛው ሕዝብ ግእዝን እንደማይችል ስለሚያውቁ እንዲህ ይላልሳ እያሉ ያወናብዳሉ «እንዘ ባዕል ውእቱ በኩሉ አንደየ ርእሶ እን ጳውሎስ ኛ ቆሮ ም ቁ» ፍችውም «ሃብታም ሲኾን እናንተ በርሱ ድህነት ባለጠጋዎች ትሆኑ ዘንድ ስለእናንተ ደሃ ኾነ» የሚል ነው እነርሱ ግን ሙሉውን ሳይጠቅሱ ቆርጠውታል ሆኖም ይህ ጥቅስ «ፈቃል በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ» ለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለውም ስለዚህም ማስረጃነቱን ለማወናበድ ካልተጠቀሙበት በቀር ምንም ማስረጃነት የለውም ማስረጃ ሊኾን የማይችለውም ነድየ የሚለው የሚስማማው ለሥጋ ነው እንጅ ለመለኮት አይደለምና ቃል ከሥጋ ጋር በተዋሐደ ጊዜ የሥጋ ንድየት በቃል ባዕልነት ተወግዷል ስለዚህ የዚህ ማስረጃነት ተቀባይነት የለውም ቀጥለውም «ስለዚህ ከእምቅድመ ዓለም ልደቱ ድ ለማድረግ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱን በመላ ተቀብሎ ከአብ ተወለደ እንጅ የቀደመ ልጅነቱስ አልተነሣውም» ይላሉ በመቀጠልም «ወልድስ በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ባይወለድ ወልድ በሰውነቱ እንደ አብ ባልገዛም አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን በመላ በሰፋ ባልሰጠውም ነበር» ብለው ወልድን ከአብ ያሳንሳሉ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በመግዛት አንድ ናቸው ይህ ምስጢረ ሥላሴ ነው ይህ የመግዛት አንድነት ወልድ ሥጋን በለበሰ ጊዜ አልተቋረጠም ስለዚህ ወልድ የመግዛት አንድነቱን ይዞ ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ሥጋን ቢዋሐድ ሥጋ የመግዛት ሥልጣንን ከወልድ ያገኛል ገንዘቡ ያደርጋልን እንጅ ከአብ አያገኝም አስቀድመን እንደተናገርነው ወልድ ባለበት አብና መንፈስ ቅዱስ አሉና አብ ለወልድ የመግዛት ስልጣንን የሚሰጠው ወልድም የመግዛት ስልጣንን የሚቀበል አይደለም ምክንያቱም ከመግዛት አንድነቱ የተለየበት ጊዜ ስለሌለ አሁንም በግእዝ ጠቅሰው ለማወናበድ «ኢይሁብ ክብርየ ለባዕድ ለተሳትፎ ወስብሐትየ ለግልፎ እን ኢሳ ምጃ ቁጆ» ይላሉ ትርጉሙን እንመልከት ፈእኔ እግዚአብሔር ነኝ ክብሬን ለሌላ ምስጋናየንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም» የሚል ነው ቆርጠው ስላስቀሩት ነው እንጅ እስኪ አስተውሉ ወገኖቼ። ወልደ አብ ገጽ ቿ ላይ ፈመንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ተሠጠ ማለት ነው መሠጠቱ ወርቅ ተመዝኖ ከብት ተቆጥሮ እህል ተሰፍሮ እንዲሰጥ እንደዚያ ተሰጠ ማለት ማለት ነውን ቢሉ እንዲህስ አይደለም እንዴት ነው ቢሉ ጥንተ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ለወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወት ኾነው ማለት ነው በእንተዝ ይትበሃል ከመ ነሥአ መንፈሰ ዚአሁ ዘተነግረ በኢሳይያስ ነቢይ እንዘ ይብል መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌየ ቀብዓኒ በእንተዝ ሰበከ እንዘ ይብል እስመ መንፈስ ዘዚአየ በህላዌ ለሊሁ ኀደረ ላዕሌየ በእንተ ዝንቱ ወለምንትኑ ተሰመይኩ መሚሐ እንበለ ዳዕሙ ሶበ ኮንኩ ሰብአ እን ሳዊሮስ ዘአንጾ ሃ አ ክ ቁ» ይላል ሙሉ ንባቡ እንግዲህ እንደተለመደው ቃል በቃል ለማየት እንሞክር ፈመንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ተሠጠ ማለት ነው መሠጠቱ ወርቅ ተመዝኖ ከብት ተቆጥሮ እህል ተሰፍሮ እንዲሰጥ እንደዚያ ተሰጠ ማለት ማለት ነውን ቢሉ እንዲህስ አይደለም እንዴት ነው ቢሉ ጥንተ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ለወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወት ኾነው ማለት ነውን በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ «ፉመንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ኾነ» የሚል ትምህርት የለም በቤተክርስቲያናችን ካሉት ምስጢራት መካከል አንዱ «ሜሮን» ነው በዚህ ሜሮን በሚባል ቅዱስ ቅብዐት ላይ መንፈስ ቅዱስ ያድርበታል መንፈስ ቅዱስ ያከብረዋል እንላለን እንጅ ረመንፈስ ቅዱስ ቅብዐ ሜሮን ነው» ብለን አልተማርንም በሐዋ ሥራ ላይ እንደምንመለከተው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ አደረባቸው እንላለን እንጅ ፈሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ሆኑ» አንልም ምክንያቱም የሚያድርባቸው በጸጋ ነውና ስለዚህ ይህ አስተምህሮ የእኛ አይደለምና በአንዲት ገዳማችን ስም እንዲህ ዓይነቱን ኑፋቄ ማውጣት ድፍረት ካልኾነ በቀር ሌላ ምን ሊባል ይችላል። የምንድንበት ይህ ነው የሚፈውሰን ይህ ነው የጎበኘን ይህ ነው» ይላል እንግዲህ ኹላችሁ እንደምታዩት ቆራርጠው በጠቀሱት ጥቅስ መንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ የባሕርይ ሕይወት ኾነው የሚል ትርጉም አንድም ቦታ ተጽፎ አላገኘንም ፈበባሕሬዬ ገንዘቤ የሚኾን መንፈስ ቅዱስ በህልውናየ ጸና ብሎ አስተማረ» ይላል እንጅ ዳግመኛ መንፈስ ቅዱስን ተቀበልሁ አላለንም ሰው ስለኾነ ይህንን ተናገረ ክርስቶስ የተባለው ሥጋና መለኮት ከተዋሐዱ በኋላ ነው እና ከተዋሕዶ በፊት ክርስቶስ አልተባለም ነበርና አሁን ግን ሲዋሐድ ክርስቶስ ተባለ ስለዚህም ሰው በመሆኑ «በእኔ ህልው ሆኖ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ በህልውናየ ጸና ለሥጋየ ገንዘቡ ኾነ» አለን እንጅ እነርሱ እንደሚሉት ዳግመኛ መንፈስ ቅዱስን ተቀበልሁ አላለንም ፈሬዳግመኛ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ» የሚሉት በወልድ ህልው ሆኖ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ወዴት ሄዶ ነው። እዚህ ላይ ማስተዋል ያስፈልገናል ዋናው የክህደታቸው ምንጭ ይህ ስለኾነ እኛ የምንለው መንፈስ ቅዱስ ለአብ እና ለወልድ የባሕርይ ሕይወታቸው ነው ይህም ጥንት ከሌለው ዘመን ጀምሮ በሰው ህሊና በማይመረመር አምላካዊ ጥበብ ማለት ነው ስለዚህ ወልድ ከሥጋ ጋር ሲዋሐድ ይህ የወልድ የባሕርይ ሕይወቱ የኾነው የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ለሥጋ ገንዘቡ ኾነ ነው እነርሱ የሚሉት ደግሞ ወልድ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ ዳግመኛመንፈስ ቅዱስን ሕይወቱ አደረገ ነው እኛ የምንጠይቀው ያ በቃል ህልው ሆኖ ይኖር የነበረው መንፈስ ቅዱስ የት ሄዶ ነው ዳግመኛ አከበረው የሚባለውን። ወይስ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አርጅቶበት ማደስ ያስፈልገዋል ልትሉን ነውን እኛ ግን አባቶቻችን እንዳስተማሩን እንመራለን ኢሳ ላይ ያለውን ቃል ሉቃ ላይ ይተረጉሙታል ሳዊሮስም ሃይማኖተ አበው ላይ እሱን ይተረጉማል ሳዊሮስ ክ ቁ እንዲህ ይላል «ስለዚህ ነገር ከዚህ በኋላ ለድኖች የምሥራች እነግራቸው ዘንድ ያዘኑትን አረጋጋቸው ዘንድ ለተማረኩት ነጻነትን እሰብክላቸው ዘንድ ዕውሮች ያዩ ዘንድ ስለዚህ ላከኝ አለ መንፈስ ቅዱስ ገንዘቡ ኾነ መባሉ ቃል ሰው ስለኾነ ነው ሰውማ ባይኾን ኖሮ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ህልው እንደኾነ መንፈስ ቅዱስ በባሕርየ መለኮት ገንዘቡ ነውና እንደምን ገንዘቡ ኾነ ይባላል አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ህልው መሆኑን እንደተናገረ» ሳዊሮስ እዚህ ክፍል ላይ የተረጎመው ኢሳ ላይ ያለውን ቃል ነው እንግዲህ ሳዊሮስ በግልጽ እንዳስቀመጠልን መንፈስ ቅዱስ በወልድ ህልው ሆኖ ይኖራል ያ ህልው ሆኖ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ወልድ ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ለሥጋ ገንዘቡ ኾነ ማለት ነው እንጅ ዳግመኛ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚል ትምህርት አላስተማረም እንዲያውም እዚሁ ክፍል ቁጥር ላይ ሊቁ ሳዊሮስ እንዲህ ይላል ፈበዚህም ግብር ተዋሕዶ ጠፍቶ ከነቢያት እንደ አንዱ አልኾነም መንፈስ ቅዱስ ያደረበት አይደለም» ይላል ስለዚህ የት ቦታ ላይ ነው ወልድ መንፈስ ቅዱስን ዳግመኛ ተቀብሎ አብ ከማኅጸነ ማርያም ወለደው የሚለው ትምህርት ያለውን። ሉቃ ላይም ወንጌላዊው ሉቃስ ኢሳ ያለውን ወስዶ አስቀምጦታል ትርጓሜ ወንጌሉ እንዲህ ይላል «ዘይብል መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌየ ዘበእንቲአሁ ቀብዓኒ» መጽሐፉን ገልጾ ሳለ ማስተማር በእኔ ህልውና ባለ መንፈስ ቅዱስ ያዋሐደኝ እግዚአብሔር አንድም ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ተርጉሞታል መንፈስ ዘዚአየ በህላዌ ለሊሁ ኀደረ ላዕሌየ ብሎ የባሕርይ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ህልው ነው ወዘበእንቲአሁ ቀብዓኒ ስለማስተማርም ያዋሐደኝ መንፈስ ቅዱስ ነዳያንን አስተምራቸው ዘንድ ላከኝ ተብሎ ተተርጉሟል ስለዚህ እነሱ ለጻፉት ኑፋቄ ይህ ማስረጃ ተብሎ ሊጻፍ አይገባውም ነበር ነገር ግን ሰውን ወደ ጥርጥር ለመክተት ተጠቅመውበታል ፈቀባ» የሚለው ቃል በርካታ ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል ተመልክተናል እዚህ ላይ ቀብዓኒ ያለውን ያዋሐደኝ ብለው ነው የተረጎሙት ስለዚህ ምናልባት ቅብዐቶች የራሳቸው ሃይማኖተ አበው የራሳቸው የትርጓሜ መጻሕፍት ሊኖሯቸው ይችል ይኾናል እንጅ የእኛ መጻሕፍት ግን ፈመንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ተሠጠ ማለት ነው መሠጠቱ ወርቅ ተመዝኖ ከብት ተቆጥሮ እህል ተሰፍሮ እንዲሰጥ እንደዚያ ተሰጠ ማለት ማለት ነውን ቢሉ እንዲህስ አይደለም እንዴት ነው ቢሉ ጥንተ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ለወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወት ኾነው ማለት ነው» ብለው አናገኛቸውም ምክንያቱም ኑፋቄ ነውና።