Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

የተቀበረ መክሊት 1.pdf


  • word cloud

የተቀበረ መክሊት 1.pdf
  • Extraction Summary

ውድ ጊዜአቸውን መሥዋዕት በማድረግ መጽሐፏን አንበው የጠመመውን አቅንተው የጎደለውን ሞልተው በማረም የረዱኝን አባቶች አቶ ሠርጽ ዕጓለ ጽዮንንና አቶ ጸጋዬ ደምሴን በአንዳንድ የትርጉም ሥራዎች ሞያዊ እገዛ ያደረጉልኝን ኤክስፐርት ዮሴፍ መኮንንን በኮምፒውተር ከመጻፍ ጀምሮ እስከ ማሳተም ድረስ ባለው ሂደት በጊዜአቸው በጉልበታቸውና በገንዘባቸው የረዱኝን ወገኖችና መጽሐፏን ሳዘጋጅ ከጎኔ ሆነው ያበረታቱኝን ወንድሞች ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው። አብዛኛዎቹ የስብከት መድረኮቿ የተሞሉት ሌላውን በመንቀፍ ወግና ሥርዓትን የሚሰብከው ቁጥር በርካታ በመሆኑም ከአምላካዊው ሕግና ሥርዓት ይልቅ የሰውን ሥርዓት አስበልጦ ይመሰከታል ይህ ሁሉ ከንቱ አምልኮ ነው። እሳት የመለኮት ምሳሌ ነው። ሰው በመሆኑ አስታራቂ ሆነን ዛይ አበ ምዕራፍ ክፍል ቁዉ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅም በኛ ድርሳኑ ከቁ ባለው ክፍል እንዲህ ብሏል ይቤ ወናቀርብ ሉቱ መሥዋዕተ ለእግዚአብሔር እመንገለ ዐራቅይናሁ መሥዋዕት ዘይቤ ፍሬ ከናፍር ውእቱ አለ ይትአመኑ በስሙ ወአሉሰ አቅረቡ አባግዐ ወአልህምተ ወንሕነኒ ኢናበውእ ምንተኒ እምእሉ ግብራት አላ አኩቴተ እስመ እግዚአብሔር ይሠምር በዘከመዝ መሥዋዕት መፍትው ለነ ናብእ ሉቱ ዘከመዝ መሥዋዕተ ከመ ያብእ ውእቱኒ ለአብ ወኢይትከህል ያቅርቡ ምንተኒ ዘአንበለ በዐራቅይናሁ ለወልድ ትርጓሜ በወልድ አስታራቂነት በኩል ለአግዚአብሔር መሥዋዕትን እናቅርብ አለ መሥዋዕት የሚለው ስለስሙ የሚመሰክሩ የክንፈሮች ፍሬ ነው። አኛ ግን ከእነዚህ መካከል ምንም ምን አናቀርብም ምስጋናን እአንሠዋለን እንጂ።

  • Cosine Similarity

ቆሻሻው ቢነሣ ሊገኝ የሚችለውን ያንን ቀደምት አባቶቹ የጠጡትን ንጽሕ ውፃም ጭምር ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያናችን መሠረተ እምነት ዶግማ ክርስትና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ የተመሠረተና የተደመደመ ፃይማኖት ነው ይህም ሲባል መሠረተ እምነቱና ዶግማውና ሥርዓቱ ቀኖናው ሁሉ በአንድም በሌላም መንገድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ማለት ነው ከሕዝብም ከአሕዛብም ወገን የሆኑትንና በክርስቶስ አዳኝነት ያመኑትን ወገኖች በማሰባሰብ መንፈሳዊት ጉባኤ የሆነችው አንዲቱ ቤተ ክርስቲያን ጌታ ለሐዋርያቱ ያስተላለፈውን እርሱ ካረገ በኋላም መንፈስ ቅዱስ መጥቶ የገለጠውን ትምህርት ዮሐ ከሐዋርያቱ ተቀብላ ስትመራበት ቆይታለች። ምክንያቱም መጀመሪያውኑ በጥሩ መልክ የተዘጋጀ ስለሆነ ያለምንም ለውጥ ለመኖር ይችላልና በተጨማሪም የኢኦተቤክ መሠረተ እምነት በአጠቃላይ በ እንደሚከፈል እፒሁ አባት በሌላው መጽሐፋቸው ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል የቤተ ክርስቲያን ዶግማ በአጠቃላይ በ ክፍል ይከፈላል ይኸውም የአግዚአብሔርን ህልውና ማወቅና ማመን ይህም ማለት እግዚአብሔር አምላክ የነበረ ያለ የሚኖር አምላክ እንደሆነ ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ አንድም የሆነ የሌለ አምላክ እንደሆ ማመን አግዚአብሔር በሦስትነት እግዚአብሔር በአንድነቱም በሦስትነቱም ጸንቶ ያለ አምላክ ስለሆነ ሦስትነቱ ሳይጠፋ በሦስትነቱም ርባኤን ሳያመጣ የሚኖር አምላክ መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅና ማመን ዓለም በጠቅላላ ሰማይና ምድር በውስጣቸው የሚገኙ ሁሉ የሚታየውም የማይታየውም የራቀውም የቀረበውም ሁሉ በአግዚአብሔር ፈጣሪነት ለተቀደሰ ዓላማ መፈጠሩን ማመን ድኅነተ ዓለም ዓለም ከተፈጠረ በኋላ በሰው በደል ምክንያት ለጥፋት ተዳርጎ መኖሩ የታወቀ ነው ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ነውና ስለታረቀው ቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድያ ልን አንደላከ ግልጥ የሆነ ክርስቲያናዊ ትምህርት ነው የእግዚአብሔር ፍጽም ፍቅር የተገለጠው በዚህ ዓለም ድኅነት ነው የዘላለም ተስፋቸውም ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን ማወቅ ምስጢረ ተዋሕዶ ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ ስለሆነ አምላክ ወስብእነቱ በተዋሕዶ መሆኑን ማመን ተገቢ ነው ይኸውም መለኮት ከሥጋ አካልና ከሥጋ ባሕርይ ጋር ሥጋም ከመለኮት አካልና ባሕርይ ጋር ተዋሕዶ አምላክ ወስብእ መባሉ ረቂቅ ምስጢር እውነተኛም ፃይማኖት መሆኑን ቤተ ክርስቲያናችንም በዚሁ ምክንያት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እየተባለች የምትጠራ መሆኗን መረዳት ምስጢረ ምጽአት ክርስቶስ ለሁለተኛ ጊቬ ወደዚህ ዓለም እንደሚመጣ ይህንም ዓለም አሳልፎ ሌላ ዐዲስ ዓለም እንደሚተካ ኦርቶዶክሳዊ እምነታችን ነው። የዘመን መቀዳደምና የክብር መበላለጥ በሌለበት በክበበ ሥላሴ ከሚገኙት ሦስት አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን የምታምነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዋ ነው ዮሐ ዞ የሐዋ ሥራ ሮሜ ቲቶ ጴጥ ቦዞ ዮሐ ቾ ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮታዊ ባሕርዩ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ የማያንስ ትክክል የሆነ የአግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ሁሉ በእርሱ የተፈጠረበት የአብ አካላዊ ቃል ነው ዮሐቦ በኃቁላና በዘላለማዊ ልደቱ ከአብ የተወለደው የእግዚአብሔር ቃል ወልድ ዋሕድ በኋለኛው ዘመን ዓለምን ለማዳን ያለዘርዐ ብእሲ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ መዝ ሳሙቁ ሉቃ ይህም ሲሆን አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይከፋፈል በመሰኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ ያለዘርዐ ብእሲ ሥጋንና ነፍስን መንፈስንም ነሥቶ በሥጋ ሥርዓት ከድንግል ማርያም በመወለዱ ደግሞ የማርያም ልጅ ነው አኮ ውእቱ ወልደ ማርያም በመሰኮት አላ ዘከመ ሥርዓተ ትስብእት በመለኮት የማርያም ልጅ አይደለም ሰው በሆነበት ሥርዓት ነው እንጂ ሃይ አበ ዘቴዎዶስዮስ ምዕራፍ ክፍል ቁ የቃል ሥጋ መሆን ምስጢር የተከናወነው በተዋሕዶ ሲሆን ይህም ተዋሕዶ ከመቀላቀል ከመጠፋፋት ወዘተ የውሕደት ዓይነቶች ፈጽሞ የተለየ እግዚአብሔር ቃልና ሥጋ የባሕርይ መደባለቅና መለወጥ እንዲሁም የአቅዋም ሽረትና ፍልሰት ሳይኖርባቸው ፈጽመው ሳይለያዩና ሳይከፋፈሉ ምንታዌን አጥፍተው በአንዱ የአካል ተዋሕዶ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ነው የተሰኘበት ምስጢራዊ መገናዘብ ነው በዚህ ተዋሕዶ የቃል የሆነው ነገር ሁሉ ለሥጋ ከኃጢአት በቀር የሥጋ የሆነው ነገር ሁሉ ለቃል ገንዘቡ ብረቱ ሆኗል ወእንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል የቃል የሆነው ነገር ሁሉ ለሥጋ ሆኗል የሥጋ የሆነው ነገር ሁሉ ደግሞ ለቃል ሆኗል እንዲል ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ባለመቀበል የኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም አምላክነትና ፍጹም ሰውነት ክዶ ወልድ በመለኮቱ ፍጡር ነው ያለውን አርዮስንና የተረገመች ትምህርቱን የተዋሕዶ ምስጢር በመለወጥ እንደተፈጸመ ቆጥሮ የክርስቶስ ሰውነት ወደ አምላክነቱ ተለወጠ የሚለውን የአውጣኬን የውላጤ ትምህርት አንዲሁም ከተዋሕዶ በኋላ በክርስቶስ ሁለት ህላዌና ሁለት ገጻት አለ የሚለውን የንስጥሮስን ክሕደትና የሌሎችንም በተዋሕዶ ትምህርት ላይ ኑፋቄ ያመጡትን ሁሉ ቤተክርስቲያን ከአንድነቷ ለይታለች። ሰው በመሆኑ መከራን ተቀበለ እንጂ ለዘለዓለሙ ሥጋን ተዋሕዶ ይኖራል አንዳለ ቅአትናቴዎስ ሃይ አበ ምዕራፍ ክፍል ቁ ስለዚህ ሞትን ድል ነሥቶ በአብ ቀኝ የተቀመጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ለዛላለምም የማይለወጥ ፍጽም አምላክ ፍጽም ሰው ነው ዕበ ዛሬ ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ በብዛት የሚሰበከው የክርስቶስ አምላክነት ለብቻው ተነጥሎ ነው። አምላክ ለምን ሰው ሆነ። ራሱ በደሙ አዳነን እንጂ ፃይ አበ ምዕራፍ ክፍል ቁ ቹዌ ኢሳ ፅቹ ፀን ግእዙን ተመልከት ስለዚህ አኛን ከእግዚአብሔር ጋር ሊሲያስታርቅና ወደ አግዚአብሔር ሊያቀርበን ሰው ሆኖ የመጣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢአት ንጽሕ የሆነ በሰውነቱ ሰውን በአምላክነቱ ደግሞ አግዚአብሔርን ሊወክል የቻለ እንደ ኦሪት ካህናት አስታራቂነቱ በሞት የማይሻር ሕያውና ዘሳማዊ ሊቀካህናት ሀነ ኤፌ ዕብ አንዱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርና ሰው ስለሆነ ተበድያለሁ የሚል እግዚአብሔርና በድያለሁ የሚል ሰው በእርሱ ተገናኙ ይህም በመካከላችን የነበረውን ጥል አስወግዶ ዕርቃችንን ፍጽም አድርጎታል በመጽሐፈ ምዕላድ የሚከተለው ተጽፎአል እምቅድመ ይሠጎ ተኀኅጥአ ንጽሕ ዐራቂ አምክልኤ ጾታ እምይእዜስ ይደልዎ ይስረይ ኃጢአተ ምስለ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ በመለኮቱ እስመ ተረከበ ንጽሐ ዐራቄ ወመተንብለ በትሰብእቱ ትርጓሜ ሥጋ ከመልበሱ በፊት በሁለቱም ወገን ንጹሕ የሆነ አስታራቂ ታጥቶ ነበር። በጌታችን መገለጥ ተወጥኖ በፈሰሰው ደሙ የጸናና እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ ያለው ጊዜ ነው ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ መሆኑን ሲገልጽ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅመኑ ውእቱ ሊቀ ካህናት ወምእመን ዘአንበሌሁ ዘይክል ለሊሁ ባሕቲቱ ሰራዬ ኃጢአት ወምንት ውእቱ መሥዋዕት ዘአፅረጎ በእንተ ዝንቱ ሥርዓት ዘእንበለ ሥጋሁ ባሕቲቱ ዘነሥኦ በእንተ ዝንቱ ግብር ትርጓሜ ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢአትን ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራቂ ማነው። ቅዱሳት መጻሕፍት እንደመሰከሩ ዮሐ ዞይ ጢሞ ዕብ ኤፌ ስለሌላው የሚጸልዩ ቅዱሳን ቢሆኑ እንኳ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡት በክርስቶስ በኩል ነው ምክንያቱም ሰው በራሱ ብቁ ሊሆን አይችልም የሰው ብቃት ክርስቶስ ብቻ ነ ነውና ኛ ቆሮ ኛ ቆሮ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የድርሰት ክፍል በ ዓም በታተመውና ጽድቀ ፃይማኖት የቤተ ክርስቲያን የፃይማኖት ውሳኔዎች በተሰኘው መጽሐፍ ገጽ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አሰለ እንዲሁም የሞቱ ቅዱሳን ከአግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ የሚያርቁን አይደሉም ከኛ ጋር አንድ ማኅበር ሆነው በክርስቶስ ፍቅርና በክርስቶስ ጸሎት የተያያዙ ናቸው እንጂ። ከዚህ በኋላም ሊያደርግ ያሰበው አሳቡ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው ኤፌ ይህን ባለመረዳት ሰው የሆነበትን ዓላማ ዘንግተው ስለቀድሞው ኃጢአታችን ከሞተልን በኋላ አሁን ለምንሠራው ኃጢአት በክርስቶስ ሳይሆን በሌሎች ነው የምንታረቀው ብለው ሌላ ዐዲስ መሠረት መሥርተዋል ነገር ግን ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም አርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ኛ ቆሮ አነዚህ ወገኖች የተሳሳተ አመለካከታቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የእግዚአብሔርን ቃል ላልተነገረበትና ላልተጻፈበት ዓላማ አንዳሻቸው ይጠቅሳሉ የተመሠረተውን አፍርሰው እነርሱ ላኖሩዋቸው ዐዳዲስ መሠረቶች ድጋፍ እንዲሆኑአቸው ከሚጠቅሱአቸው መካከል የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ የሚለው ይገኝበታል ኛ ቆሮ ከዚህ ቃል የምንረዳው ሐዋርያት ወንጌልን በመስበካቸው ምክንያት ስለተከናወነውና ዛሬም በሕይወተ ሥጋ ባሉት ሐዋርያትና ሰባኪያነ ወንጌል እየተከናወነ ስላለው የሰውና የእግዚአብሔር ዕርቅ ነው ሐዋርያቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ባኖረው የማስታረቅ ቃል ለሰው ወንጌልን በመስበክ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምኖ ንስሐ በመግባት በክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቅ የሚያደርጉት ይህ የማስታረቅ አገልግሉት ትርጉሙ ይኸው ብቻ ነው በዚህ ምፅራፍ ቁ ዐ ላይ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ የሚለውን በእኛ እንደሚማለድ በሚለው በመተካት የእግዚአብሔርን አሳብ ወደ ራሳቸው ፍላጎት ለማምጣት ጥረት ያደርጋሉ። እነርሱ እንደሚያስቡት በቪህ ምክንያት የክርስቶስ አምላክነት አይዋረድም ይልቁንም ሰው መሆኑ ይገለጣል እርሱ ለዘለዓለም ፍጽም አምላክ ፍጽም ሰው ነው በክርስቶስ ፍጹም ሰው መሆን ቀድሞ የተከናወነውንና ዛሬም እስከ መጨረሻው የሚከናወነውን ቀጥሎ እንመለከታለን ኢየሱስ ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት እግዚአብሔር በቅዱስ ቃሉ ውስጥ እንደገለጸው ለዐዲስኪዳን ጥላና ምሳሌ ሆኖ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሕዝቡን ሲያስተዳድርና ሲመራ የኖረው በሕዝቡና በእርሱ መካከል መካከለኛ አድርጎ ባቆማቸው ተቀብተው በተሾሙ ካህናት ነቢያትና ነገሥታት አማካኝነት ነበር። በዚህ ክፍል ግን ስፍራ ሰጥተን በስፋት የምንመለከተው ሊቀ ካህንነቱን ነው ሊቁ ቄርሎስ በዛይማኛተ አበው ም ክፍል ቁ ላይ እንደመሰከረው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው በመሆኑ ብእሲ መሲሕ ኢየሱስ ታቦት አስታራቂ ለሙታን በኩር ከሙታን ወገን ለሚኑሣም በኩርየቤተ ክርስቲያን የምእመናን ራስ ተብሏል በነዚህ ስሞችም ይጠራል እርሱ ፍጽም አምላክ ብቻ ሳይሆን ፍጽም ሰውም ነውና ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን ቢመስልም ዕብ የአምላክነቱ ክብር ለቅጽበት እንኳ አልተቀነሰም። ነገር ግን ክርስቶስ አምላክም ሰውም በመሆኑ በሰውነቱ ሞቶ በአምላክነቱ ኃይል ተነሣ ጴጥ አንስ አአምን ከመ ውእቱ ሞተ በሥጋ ወሐይወ በኃይለ እግዚአብሔር እኔ በሥጋ እንደሞተ በእግዚአብሔርነቱ ኃይልም እንደተነሣ አምናለሁ እንዳለ ቄርሎስ ሃይ አበ ም ቁ እንደዚሁም በአምላክነቱ ኃጢአትን ሁሉ የሚያስተሰርይ ሲሆን ሰው በመሆኑ ደግሞ የዐዲስ ኪዳን አስታራቂ ሆኗል ወውአቱ መዋዔ ኩሉ ኃጢአት በመለኮቱ ኮነነ ሊቀ ካህናት በትስብእቱ በመለኮቱም ኃጢአትን ሁሉ የሚያጠፋ እርሱ ሰው በመሆኑ አስታራቂ ሆነን ዛይ አበ ምዕ ክፍ ቁ በፍጹም ሰውነቱ የክርስቶስ የአስታራቂነቱ ግብር የተገለጸው በሊቀ ካህንነቱ ነው የሊቀ ካህንነቱን ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ተጽፎ የምናገኘው በዐዲስ ኪዳን ክፍል በተለይ በዕብራውያን መልእክት ውስጥ ነው። ሞቶ የተነሣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በአብ ቀኝ ተቀምጦአል ስለኛ ይከራከራል ሮሜ ምልጃ ዕርቅና ሰላም ዓም ገጽ በኛ ዮሐ ላይ ወእመኒ ቦ ዘአበሰ ጳራቅሊጦስ ብነ ኀበ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህም ማለት የበደለ ሰው ቢኖር ከአብ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃ አለን ማለት ነው ነገር ግን የግእዙ ኋራቅሊጦስ ብነ ያለውን በአማርኛ ዐዲስ ኪዳን ትርጉማቸው ላይ ጳራቅሊጦስ አለን በማለት የክርስቶስን ጠበቃነት ለማስካድ ተሞክሯል። ይህም ሰው ስለመሆኑ እንጂ ለሌላ አልተነገረም እሱ የባሕርይ አምላክ ሲሆን ሰው በመሆኑ ከአብ ክብርን ይቀበላል ሃይ አበ ም ክፍል ቁ እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ነገር አለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሁላችን በመሞቱ አንድና ሕያው መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አንድ ጊዜ ለዛለለም አቅርቧል። አምላክ የሆነ ቃል እንደኛ ሰው ሆኖ በዐዲስ ሥራ ታየ። ሊቀ ካህናት በመሆኑ ያን ጊዜ ይማልድላቸዋል አለ ለዘላለም ሕያው ስለሆነ ለዘወትር ያድናቸው ዘንድ ይችላልና አለ ከእርሱ በኋላም የሚተካ የለም የዮሐንስ አፈወርቅ ኛ ድርሳን ቁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሊቀ ካህንነቱ የዐዲስ ኪዳን ብቸኛና ብቁ የሆነ አስታራቂ መሆኑን ስናስብ ብቃቱ የተለካባቸውን መስፈርቶች ማስተዋል ይጠበቅብናል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF


Download options | Convert to Pdf | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact