Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

የፈቃዱ ምስጢር 2.pdf


  • word cloud

የፈቃዱ ምስጢር 2.pdf
  • Extraction Summary

» በፍጥ አለች መልአኩም ለማርያም ጌታ ከአንቺ ጋር ነው» አላት መጀመሪያ የደረሳት መልእክት እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር መሆኑ ነበር።» ማቴ በሌላ አንጻር ደግሞ ሰው መንፈሳዊ በረከትና በሰማያዊ በረከት ውስጥ ከምድራዊ እስራት ፈጽሞ ስለምንፈታ ነፃ እንወጣለን ሰው ካለው ነገር በላይ መሆን ካልቻለ በምድራዊ ነገር ባለጸጋ ቢሆንም እንኳ በረከትን ገና አልተለማመደም እውነተኛ በረከት ምንም ዓይነቱ ስንኩል ምክንያት ሳንሰጥ በሙሉ ልብ መታዘዝ ያስችለናል ፈቃዱን ለመፀነስና ለመውለድ የሚያስችል ይህ ዓይነቱ በረከት የእግዚአብሔር ህልውና ወይም መገኘት ውጤት ነው።

  • Cosine Similarity

በእርሷ የሚሆነውን የእግዚአብሔርን ዓላማና አሳብ ከመንገሩና ከመግለጹ በፊት ጌታ ከእርሷ ጋር እንደሆነ አስረግጦ አበሠራት ብዙውን ጊዜ የምንቸገረው ማን ከእኛ ጋር እንዳለ ስለማናውቅ ነው የነገሥታት ንጉሥ ግን ከእኛ ጋር ነው ጌታ ከእኛ ጋር ሲሆን የሚመጣው ነገር ሁሉ በረክት ነው ፈቃዱም ሳይከለከል ይከናወናል ማርያምን ለታላቅ የእግዚአብሔር ዓላማና አሳብ ሊያዘጋጃት የቻለው የእግዚአብሔር ህልውና መገለጥ ነው ጌታ ከእርሷ ጋር መሆኑን መስማት ለአንዲት ልጃገረድ በዚያን ዘመን ቀላል ነገር አልነበረም የተቀበለችው ሰላም ደስታና ጸጋ ራሱ ካሰበችውና ከገመተችው ሁሉ በላይ ነበር ትጠባበቀው የነበረ ነገር አልነበረም ይህ ሁሉ የሆነው በአግዚአብሔር ስለታቀደ ብቻ ነበር ማርያም በጸጋ መሞላቷን በራሷ አላስተዋለችውም ሁሉን ያከናወነላት እግዚአብሔር ነው በጸጋ መሞላት ለእግዚአብሔር ሥራ እኛን ብቁ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የእርሱ ማንነት በአኛ እንዲገለጽ ያደርጋል የእግዚአብሔር ህልውና የሚገለጸው የእርሱ ጸጋ በሚሠራበት ቦታ ነው ጸጋ በሙላት አንዲሠራ ለግለሰብ ይህን ነፃ ስጦታ መቀበል ወደ ሙሉ ፈቃድ የመግቢያው መንገድ ነው የጸጋውን ሙላት በእምነት መቀበል ለእግዚአብሔር ሥራ እኛን ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን የክብሩ መግለጫ ለመሆንም ያስችላል እግዚአብሔር ማንነቱን የሚገልጸው በጸጋ ውስጥ ነው ስለዚህም ነው ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ «ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ ዮሒ ተብሎ የተጻፈው በጸጋው ሙላት ውስጥ ራሱን ገለጠ በመካከሳችንም ተመላለሰ ከዚህ የተነሣ በአባቱ ዘንድ የነበረውን ክብሩን አየን ጸጋ ክብሩ እንዲገለጥ መንገድ ያዘጋጃልና መልአኩ ማርያምን ጌታ ክአንቺ ጋር ነው» ሲላት እግዚአብሔር በእርሷ ውስጥ ከመገለጡ በፊት ለአርሷ መገለጡን እያበሠራት ነበር «ጌታ ከአንቺ ጋር ነው» የሚለው አዋጅ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ የያፅቆብ አምላክ ማለትም የቃል ኪዳን የበረከት የተስፋና የብርፃናት አምላክ በኃይሉ በጥበቡ በቅድስናው በበጎነቱ በክብሩ በግርማው በአስፈሪነቱ ከአንቺ ጋር ለመሥራት መጥቶአል ማለት ነው ይህ የእግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር መሆን ለባሪያዎቹ ራሱን መግለጡ በብሉይ ኪዳን በቀላሉ የሚታይና የሚታመን ነገር አልነበረም እግዚአብሔር ከሰው ጋር መሆኑ የሚገለጸው ያ ስው ለታላቅ ነገር ሲለይ ብቻ ነው ለምሳሌ ያህል ጌዴዎን የእስራኤልን ሕዝብ ነፃ ለማውጣት ድፍረት እንዲኖው ጌታ ከአንተ ጋር ነው» ተብሎ ተነገረው መላ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በመሆኑ ምንም እንኳ ደካማና ፊሪ ሰው ቢሆንም ኃያል ሰው ተባለ የእግዚአብሔር መገኘት ተፈጥሮን ይለውጣል ደካማን ብርቱ ያደርጋል ሞኙን ጥበበኛ ያደርጋል መናገር የማይችለውን ታላቅ ተናጋሪ ያደርገዋል ጸ ተጠራጣሪውን ባለ እምነት ያደርገዋል ዮሐ ሕፃኑን አዋቂ ያደርጋል ኤር አግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ስለ ነበረ አሸናፊ ሰው ከመሆኑም በላይ ሁሉም ተከናወነለት እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር ኛ ሳሙ ስለዚህ የእግዚአብሔር ከሰው ጋር መሆን ግለሰቡን ከመለወጡም በላይ ሁኔታው ለዚህ ሰው ሲል ለበጎ ይለወጣል እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር በመሆኑ አስፈሪውን ጎልያድን ገደለ ከሳዖልም ጦር አመለጠ የእግዚአብሔርን አሳብ በማገልገል አምላኩን አስከበረ ለሕዝቡም ታላቅ በረከት ሆነ በዮሴፍም ሕይወት የምናስተውለው ይህንኑ ነው እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ስለ ነበረ ዮሴፍ ባለፈበት ሁኔታ ውስጥ ሁሉ መከናወንን አገኘ ታላቅ በረከትም ሆነ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ» በሸፍጥ እግዚአብሔር በዮሴፍ ምክንያት ግብጻዊውን ባረከው የአስረኞችን እንቆቅልሽ ፈታላቸው ለፈርዖን ግራ መጋባት መልስ ሆነ የራሱን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ ከረኃብ ሞት አዳነ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የመሆኑ ምልክት ለሌሎች መባረክ ምክንያት መሆናችን ነው እግዚአብሔር ጥሪውን ተቀብለው በጸጋው እርሱን ለማስከበር ከተለዩት ነቢያት ሁሉ ጋር ነበር በስደታቸውና በመከራቸው አልተለያቸውም ነበር ወደ አዲስ ኪዳንም ስንመጣ እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረው በዚህ ተስፋው ነው ስለ ጌታ ኢየሱስ የተነገረው ትንቢት ስሙ አማኑኤል ተብሎ እንደሚጠራ ነበር ኢሳ ብ አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ስለሆነ የሚያሳየው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከሕዝቡ ጋር መሆኑን ነው ይህን ተስፋ ተጨባጭ ለማድረግ ነበር ቃል ሥጋ ሆኖ በሕዝቡ መካከል የኖረው ቃል ሥጋ ሆኖ የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ በመጣ ጊዜ የሕይወቱና የአገልግሎቱ ምልክት የእግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆን ነበር ይህንን ሲያጠቃልል ሐዋርያው ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ አስተዋሽነት እንዲህ በማለት ይገልጸዋል «እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና» የሐዋ እንግዲህ ጌታ ኢየሱስን ለሥራው ብቁ ያደረገው የእግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆን ነበር የሐዋርያትም አገልግሎት ትልቁ ምልክቱ የእግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር መሆን ነበር እነርሱ ያስተላለፏቸውን መልእክቶች በምልክት ያጸና ነበር «እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ስበኩ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር» ማር ከትንሣኤ በኋላ ሥልጣን ሁሉ እንደ ተሰጠው ከነገራቸው በኋላ የገባላቸው ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እንደሚሆንና እስከ መጨረሻ እንደማይለያቸው ነው እነሆም እኔ አስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ» ማቴ አላቸው መንፈስ ቅዱስንም የላከው ይህን ተስፋ ለመፈጸም ነው እግዚአብሔር ከሰው ጋር መሆኑ የሚያረጋግጠው በእርሱ ታላቅ ነገር መከናወኑ ብቻ ሳይሆን የፈቃዱን መፈጸም ነው እንግዲህ ለሕይወትም ሆነ ለአገልግሎት እርሱን ለሚፈልጉት ጌታ የሰጠው ታላቅና ከሁሉም በላይ የሆነው ዋስትና የእርሱ ከእኛ ጋር መሆንና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በእኛ ውስጥ መኖሩ ነው ስለዚህ ነው በድፍረት «ልጆች ሆይ እናንተ ከአግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና» ኛ ዮሒ ቱብ የምንለው በእኛ ውስጥ ያለውን ታላቅነትና ኃያልነት ከተረዳን ውጫዊ ተቃውሞ አያስፈራንም ጎልያድም አያስጨንቀንም ተራራዎችም አያቆሙንም እርሱ ተራራውን ደልዳላ ሜዳ ያደርገዋልና ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ወይም ይቻላል። የሚለውን ጥያቄ የሚመልሰው ይኸው እውነት ነው ስለዚህ ለማርያም የተሰጣት መልእክት ከሁሉም አስቀድሞ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር መሆኑ ነበር እንግዲህ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ፈቃዱ ሙሉ በሙሉ በሕይወታችን ይከናወናል እንዴትና መቼ ለሚሉ ጥያቄዎች የምንፈልገውን መልስ ባናገኝም የእግዚአብሔር መገኘት ካለ ነገሩ ሆኖአል ተከናውኗልም ማለት እንችላለን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ የእርሱ ሥራ በጐልሕ ስለሚታይ ጐድጓዶቻችንን እየዘጉ ራቁልን ያሉ ሁሉ ተመልሰው መጥተው እንደ ይስሐቅ ቃል ኪዳን እናድርግ «አግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን» በፍጥ ይላሉ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ተስፋችንን እንወርሳለን ለሌሎቹም ርስታቸውን እንዲወርሱ እንደ ኢያሱ ምክንያት እንሆናለን ማስታወቂያም ሳናወጣ ሌሎች የእግዚአብሔርን ከእኛ ጋር መሆን አይተው ይመሰክራሉ «እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበረ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ወጣ» ኢያሱ ይ የአግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆን እንደ ሳሙኤል መልእክታችንን ሕይወት ያለው ከማድረጉም በላይ ሕይወታችንን በምሳሌነት የሚታይ ያደርገዋል «ሳሙኤልም አደገ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ ከቃሉም አንዳች በምድር ላይ አይወድቅም ነበር» ኛ ሳሙ የእግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆን እግዚአብሔርን ለሚወዱት ታላቅ ደስታን እግዚአብሔርን ለሚጠሉት ደግሞ ታላቅ ፍርሀትን ያመጣል በኛ ላሙ በአዋጅ አማካይነት በማርያም ሕይወት የሆነው ይህ ነበር የእግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆን የእርሱ የሆነው ውስጣችንን ስለሚሞላው የምንናገረው የእርሱን እውነት ብቻ ይሆናል የምናልመውና የምናስበው የእርሱን አሳብ ይሆናል የምንኖረውም ለእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ሕይወታችን የእርሱን ክብርና ማንነት አዘውትሮ ያንጸባርቃል በዚህ ውስጥ የምንረዳው እግዚአብሔር ከማርያምም ሆነ ከእያንዳንዳችን ጋር የሚሆነው በብቃታችን ምክንያት ሳይሆን ለእርሱ ዓላማ በጸጋውና በምሕረቱ ብዛት ስለለየን ብቻ ነው ይህን ማስተዋል በአምልኮ ያንበረክከናል በምስጋናም ይሞላናል በውስጣችን ተፀንሶ የሚወለደው መልካም ነገር ሁሉ እርሱ ከእኛ ጋር በመኖሩ ብቻ ሳይሆን በውስጣችንም ስላለ ነው ጌታ ከአንቺ ጋር ነው» ስለዚህ የእግዚአብሔር ዕቅድ ሁሉ ይከናወናል የእግዚአብሔር ህልውና ወይም መገኘት ዕረፍትን ስለሚያመጣ የበኩር ልጂን እስክትወልድ ወይም የእግዚአብሔር ፈቃድ እስኪከናወን ድረስ በፍጹም ሰላም ተሞልታ ሁሉንም ነገር በልቧ ጠበቀች እግዚአብሔር ለባሪያው ለሙሴ የገባው ቃል ኪዳን እግዚአብሔርም እኔ ከአንተ ጋር እፄዳለሁ አሳርፍህማለሁ አለው» የሚል ነው በማርያምም ሕይወት ይህ ታይቶአል መገኘቱን በሚጠሙት ባሪያዎች ሕይወት ሁሉ የሚገለጽ እውነት ነው ይህ እውነት ነው «አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉውን አልፈራም» የሚያሰኘን የእርሱ መገኘት በእምነትና በተስፋ ስለሚሞላን በመንፈሳዊ ድፍረት መኖር እንጀምራለን እርሱን እንጂ ሁኔታውን ስለማንመለከት ከአካባቢው ሁኔታ በላይ አንሆናለን ጌታ ከእኛ ጋር መሆኑን ከተቀበልን አይቻልም አይሆንም አይደፈርምም የሚባል ነገር የለም ጌታ ከማርያም ጋር ስለ ነበረ ያለ ወንድ ልጅ ወለደች ጌታ ከሙሴ ጋር ስለ ነበረ ቀይ ባሕር ተከፈለ የአራት መቶ ሠላሳ ዓመታት የባርነት ቀንበር አበቃ እግዚአብሔር ከአስቴር ጋር ስለ ነበረ በንጉሠ ፊት ሞገስ አገኘች የእግዚአብሔርን ሕዝብ ጠላት በማጋለጥ የአግዚአብሔርን ሕዝብ ከሞትና ከጥፋት አዳነች የጠላትንም ንብረት ወረሰች እግዚአብሔር ከሳምሶን ጋር ስለ ነበረ አንበሳን ገድሎ ሊበላው ከመጣው አውሬ ውስጥ የሚያበረታ ማር በላ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ጠላት አስጨነቀ እግዚአብሔር ከዳንኤልና ከጓደኞቹ ጋር ስለ ነበረ የአንበሶች አፍ ተዘጋ የእሳትም ኃይል ጠፋ እግዚአብሔር ከነቢያቱ ጋር ስለነበረ በእግዚአብሔር ልብ ያለውን መልእክት ተቀብለው አስተላለፉ ነገሥታትን አንቀጠቀጡ እሳት ከሰማይ አወረዱ ሰማያትን ዘጉ ከፈቱም የእግዚአብሔር መገኘት የተጠራንበትን እንደ ማርያም እንድንፈጽም እኛን ከማስቻሉም በላይ ሕይወታችንን አስተሳሰባችንን አመለካከታችንን አሠራራችንንና አኗኗራችንን ይለውጠዋል የአርሱ ክብርና ማንነት ስለሚገለጽ ከክብር ወደ ክብር መለወጥ ብቻ ሳይሆን የኃይሉም ታላቅነት ስለሚገለጥ «በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና» ኛ ቆሮ የእርሱን መዓዛ እያሸተትን ፈቃዱን እንፈጽማለን የጌታ ህልውና ወይም ከእኛ ጋር መሆን ለተስፋችን ሁሉ ሕይወትን ይሰጠዋል ወደ ፍጻሜም ያደርሰናል ኤልሳቤጥ ለማርያም ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት» ሉቃ ያለቻት ለዚህ ነበር ጌታ በማንነቱ ከእርሷ ጋር ነውና የፈቃዱ ምሥጢር በሕይወቷ ውስጥ በሙላት ተገሰጸ። ው ለጅ ዕፊፇቻ መጓዕ ዖታባረያጃ » ጎም» ሪኦቃ ፉረያ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና የተባረክሽ ነሽ ተባለች እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆነ ሰው በርግጥም የተባረከ ነው እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ሲሆን እርሱን ተከትሎ የሚመጣው በረከት ነው «በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ» ኤፌ የተባረከ ሰው ቋንቋው አስተሳሰቡ አካፄዱና አመለካከቱ የተለወጠ ነው የእግዚአብሔር በረከት የሚጀምረው በመንፈሳዊ ለውጥ ነው ምክንያቱም የተለወጠ ሕይወት ከርግማንና ከኃጢአት ይለያል ሕይወትን ከሚያቆሽሽ ነገርም ያሸሻል «ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ» ሲላት በሕይወቷ አማካይነት የሚገለጽ ነገር አለ ማለት ነው እግዚአብሔር ይህንን ታላቅ የበረከት የምስራች ለማርያም ሲልክላት የዛሬ ኑሮዋን ብቻ ሳይሆን ዘመኗን ሁሉ የሚለውጥ መልእክት ነበር እግዚአብሔር ከአርሷ ጋር መሆኑን ሲያረጋግጥላት ከመመረጥም አልፎ በሴቶች ሁሉ መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት ከሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች መሆኗን ስትሰማ ይህ አስደናቂ ነገር ነው ይህ ዓይነት በረከት ለእግዚአብሔር ዓላማና ፈቃድ የሚለይ በረከት ነበር የእግዚአብሔር ፈቃድ ምሥጢር በሕይወታችን እንዲከሠት የሚያደርግ ነው አግዚአብሔር ማርያምን ባርኮ ቀደም ሲል ለራሱ ለይቶ ክብሩን ከገለጸባቸው ሰዎች ጋር አደባለቃትፈ አብርሃምም ለአግዚአብሔር በመለየቱ ቃል ኪዳን ከመቀበሉም በላይ እንደሚባረክና ለዓለም ሁሉ በረክት እንደሚሆን ታወዉጀ «እግዚአብሔርም አብራምን አለው ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ አኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ታላቅ ሕዝብም አደርግሣለሁ እባርክሃለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ ለበረከትም ሁን የሚባርኩህንም አባርካለሁ» በፍጥ ስለዚህ መልአኩ «በሴቶች ሁሉ መካከል የተባረክሽ ነሽ» ሲላት ያረጋገጠላት የአብርፃምን ቃል ኪዳን ወራሽ መሆኗን ብቻ ሳይሆን ይህን የተስፋ ቃል ለመፈጸም መመረጧንም ጭምር ነበር ከሴት ሁሉ መካከል የተባረከች ያደረጋት የእግዚአብሔር የበረከትና የቃል ኪዳን ተስፋ በእርሷ በኩል ተጨባጭ እንዲሆን ለዚህ መለየቷ ነበር ሰውን ለእግዚአብሔር አሳብና ዓላማ ብቁ የሚያደርገው ከእርሱ የሚመጣ በረከት ብቻ ነው ርግማን የዚህ ተቃራኒ ነው ርግማን ለእግዚአብሔር አሳብ ዕንቅፋት ነው ስለዚህ ነው በ ተ ተተትሱኑኤሌ ኑእእኑእኑሱዑሱፁኩፒዮፐዯፓ ቢፐ የእግዚአብሔር ዓላማ ለፈቃዱ ለፈጠራቸው ሁሉ በረከት የሆነው የእግዚአብሔር ዓላማ የልጆቹ መባረክ ነው አግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን ከፈጠራቸው በኋላ የአገልግሎት ኃላፊነት ከመስጠቱ በፊት በአንድ ላይ ባረካቸው እግዚአብሔርም ባረካቸው እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም የባሕርንም ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው» ፍጥ ይህ በረከት ነው እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ላለው ኃላፊነት ብቃትን የሰጣቸው የአዳምና የሔዋን በኃጢአት መውደቅ የበረከትና የኃይል የብቃት ዕጦት ሳይሆን እንቢተኝነት ነበር በምዕራፍ አንድ ላይ እንደ ባረካቸውና ሥልጣንን እንደ ሰጣቸው እናነባለን በምዕራፍ ላይ አዳም ለእንስሶች ሁሉ ስም እንዳወጣላቸው እናስተውላለን በዚህ በረከት አማካይነት ሁሉንም አስገዛለት በፍጥረት ሁሉ ላይ ሥልጣንን ሰጠው መዝ በዚህ ሥልጣን የኖሩት በእንቢተኝነትዙ ኃጢአትን በመሥራት በረከታቸውን እስከ አጡበት ጊዜ ድረስ ነበር ኃጢአት በበረከት ፈንታ ርግማንን አመጣ ርግማን የኃጢአት ፍሬ ነው አዳም ኃጢአት በመሥራቱ ምድር ተረገመች ከዚያን ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በረከት እንዲሁ የሚሰጥ ሳይሆን በሰው ምርጫና በእግዚአብሔር ምሕረት መሠረት የምንቀበለው ነው በአዲስ ኪዳን ወደዚህ በረከት የምንገባው የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀብለን ልጆቹ በመሆን ነው በብሉይ ኪዳንም ቢሆን ይህ በረከት የሚገኘው በመታዘዝና የንስሐ ምልክት የሆነውን መሥዋዕት በማቅረብ ነው ነቢዩ ኢሳይያስ ለእግዚአብሔር ሕዝብ «እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል የአግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና» ኢሳ ያላቸው ለዚህ ነበር የምድራዊ በረከት መሠረቱ መንፈሳዊ በረከት ውስጥ ገብቶ መኖር ነው እግዚአብሔር ስለ በረከት ሲናገር ከመንፈሳዊ ነገር ቢጀምርም የእግዚአብሔር በረከት በመንፈሳዊ በረከት ብቻ የሚወሰን አይደለም የእግዚአብሔር በረከት በመንፈሳዊ በረከት የሚጀምርበት ዋና ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ስለሚያገናኝ ነው ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ከሌለው ምድራዊ በረከት ሁሉ ቢኖረውም ከርግማን በታች ነው ስለዚህ የእውነተኛ በረከት ምንጭ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን መንፈሳዊ ግንኙነት ነው ከዚህ የተነሣ ጌታ ኢየሱስ «ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል» ብሏል ማቴ ዕጋ በብሉይ ኪዳን ውስጥም ቢሆን እግዚአብሔርን ቢታዘዙ የምድርን በረከት እንደሚበሉ ደጋግሞ ነው የተነገራቸው በጸ ዐ ይሁን እንጂ እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ነገር በመንፈሳዊ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው በምድራዊ ነገር አይበለጽግም ማለት እንዳይደለ ነው በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከኃጢአት ርግማን በታች ሆነው ሳለ በሥጋ የበለጸጉ ብዙ ሰዎች በዓለም ላይ አሉ ይሁን እንጂ ብልጽግናቸው በጣም ጊዜያዊ ከመሆኑ የተነሣ ምንም የዘለቄታ ትርፍ የለውም ይህን ግልጽ ሲያደርግ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ይላል «ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል። ታጓሳና ለታፖፉፍሪጋ ታዶ ጴመፇህ ማርያም ሞገስ ያገኘችው በጌታ ስለ ተባረከች ነው የእግዚአብሔር በረከት ሞገስን ያመጣል ያበዛልም ሞገስ ማግኘቷ በአግዚአብሔር ዓይን የከበረች መሆኗን ያሳያል ስለሆነም ሞገስ ሸፍኗታል ማለት ነው ሞገስ የሚለው የአማርኛ ቃል በብሉይ ኪዳንም ውስጥ ሆነ በአዲስ ኪዳን ከእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ ጋር የተያያዘ መሆኑን እንረዳለን ሞገስ ከእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ የተነሣ በሰው ሕይወት ውስጥ የሚገለጽን የእግዚአብሔር ቀ መልካምነት ቀ በጎነት ቀ ማክበር ቆቀ ክብር ቀ ተቀባይነት ቀ ተወዳጅነት ቆቀ መወደድ ቀ ውበት ቀቆ ግርማ ቀ ብጽዕና ቀ በረከት ወዘተ ያጠቃልላል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከመቶ ጊዜ በላይ ይህ ቃል ተጠቅሷል የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ማርያም ተልኮ ሲመጣ ይህንን ሁሉ ነበር ይዞ የመጣው ለፈቃዱ ምሥጢር የሚያበቃ ሞገስ አግኝተሻል አላት በመልካምነቱ አስቦሻል «በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻልና» ሲላት እግዚአብሔር ከምሕረቱና ከዘላለማዊ ርኅራቴው የተነሣ ዓላማውንና ፈቃዱን በሕይወቷ መፈጸም ስለ ወደደ በመልካምነቱ በበጎነቱና በቸርነቱ አስቦሻል ማለቱ ነበር የእርሱ ሰላም ደስታ ሐሜት ጸጋ ህልውና በረከትና መልካምነቱ በሕይወት እንዲገለጽ ሞገሱን አለበሳት የእግዚአብሔር ሞገስ በእርሱ መልካምነትና ቸርነት ይገለጻል ሙሴ «አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ ከዚህ አታውጣን በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል። » ያለው ይህን ስላስተዋለ ይሆናል ዘጸ ዱ የእርሱ ህልውና ነው ሞገስን የሚያለብሰው ቸርነትንም የሚያበዛው እግዚአብሔር ሲመልስለት «አግዚአብሔርም ሙሴን በፊቴ ሞገስ ስላገኘህ በስምህም ስላወቅሁህ ይህን ያልኸውን ነገር አደርጋለሁ አለው» ጸ ከዚህ በኋላ ነበር ሙሴ እግዚአብሔር ክብሩን እንዲያሳየው የጸለየው «እርሱም እባክህ ክብርህን አሳየኝ አለ» ጸ ያለ እግዚአብሔር ሞገስ የእርሱን ክብር ማየት አይቻልም የእርሱ ክብር በእኛ ላይ መሆን ግርማንና ውበትን ያመጣል በአርሱ ማንነት መሸፈን ወደ ማንነቱ እኛን ከመለወጡም በላይ እርሱን እንድናንጸባርቅ ያስችሰናል እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም ሥጋ በሆነ ልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው» ኛ ቆሮ እውነተኛ ሞገስ የመንፈሳዊ ውበትም መለኪያ ነው የሙሴም ፊት ያንጸባረቀው የእርሱን ውበት ለመግለጽ ሳይሆን በእግዚአብሔር ባርያ ላይ የወረደውን የእግዚአብሔር ግርማና ሞገስ ለማሳየት ነበር ይህ ሂደት ነው ለፍጹም የፈቃዱ ምሥጢር የሚያበቃው ይህ በሙሴ ላይ የነበረው የእግዚአብሔር ሞገስ የአምላኩን መልካምነት በጎነትና ቸርነት ሁሉ ነበር ወደ እርሱ ያመጣው «እግዚአብሔርም እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ የእግዚአብሔርንም ስም በፊትህ አውጃለሁ ይቅርም የምለውን ይቅር እላለሁ የምምረውንም እምራለሁ አለ» ከጸ የእርሱን ስም በሕይወታችን እያከበርን ፈቃዱን ለማድረግ የሚያስችለን ይህ መልካምነቱ ነው ለማርያም የመጣው መልእክት ይህንን ያዘለ ነበር ሞገስ ማግኘቷ ለፍጹም መልካምነቱና የስሙን ክብር ለመሸከም አበቃት በኋላ በአምልኮዋ ውስጥ ረ ስሙም ቅዱስ ነው» ሉቃ ብላ የዘመረችው ለዚህ ነበር ተቀባይነት አግኝተሻል የእርሱ ሞገስ ምሕረትንና ተወዳጅነትን ስለሚያለብሰን በሥራችን ሳይሆን እንዲሁ እርሱ ፊት ተቀባይነትን ይሰጠናል ሰው በአምላኩ ፊት ሞስን ካላገኘ ተቀባይነት ስለማይኖረው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማከናውን አይችልም ጌታ ኢየሱስ በሞገስ ያድግ ስለ ነበረ በአምላኩ ፊት ተቀባይነት በማግኘት ፈቃዱን ለማከናወን ቻለ እግዚአብሔር አብም በአደባባይ ስለ ተቀባይነቱ ሲመሰክር እንዲህ አለ «የምወድህ ልጄ አንተ ነህ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ» ማር በዚህ አዋጅ ውስጥ ጌታ ኢየሱስ በሞገስ ተቀባይነትን ማግኘት ብቻ ሳይሆን እንደ ተወደደና እግዚአብሔር በእርሱ ደስ እንደ ተሰኘ ተመሰከረለት ከዚህ በኋላ ነው ጌታ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ እንደ ቀባው በመመስከር የጠላትን ፈተና አሸንፎ የአደባባይ አገልግሎቱን የጀመረው ስለዚህ ወደ ሙሉ ፈቃድ ውስጥ ገብተን ጥሪያችንን ለመፈጸም እንደ ማርያም በሞገሱ ተቀባይነት ማግኘት አለብን የአስቴርም ሕይወት ይህንኑ ነበር የሚያንጸባርቀው አስቴር ነገሩን ባታውቅም እግዚአብሔር እንደ ማርያም ለታላቅ ነገር አዘጋጅቷት ነበር የእርሱ ፈቃድና አሳብ በሕይወቷ ይከናወን ዘንድ ሞገሱን አለበሳት ለንግሥትነት ተመርጠው ከመጡት ሁሉ መካከል አስቴር በሄፄጌ ፊት ሞገስን አገኘች «ቆንጆይቱም ደስ አስኘችው በእርሱም ዘንድ ሞገስ አገኘች » አስቴ ከዚህ ሞገስ የተነሣ ጥንቃቄ ተደረገላት ወደ ንጉሥ በገባች ጊዜ «ንጉሥጮም ከሴቶች ሁሉ ይልቅ አስቴርን ወደደ በዓይኑም ከደናግል ሁሉ ይልቅ ሞገስንና መወደድን አገኘች የመንግሥቱንም ዘውድ በራስዋ ላይ አደረገ በአስጢንም ፋንታ አነገሣት» አስቴ ይህ ሁሉ የተጠራችበትን የአግዚአብሔርን ፈቃድ ለማከናወን ወደምትችልበት ቦታ የሚያደርሳት ሂደት ነበር የእግዚአብሔር ሞገስ በርን ይከፍታል ሁኔታንም ያመቻቻል በአስቴር ላይ የነበረው ሞገስ እያደገና እየጨመረ ስለ ፄደ «ንጉሥም ንግሥቲቱ አስቴር በወለሉ ላይ ቆማ ባየ ጊዜ በዓይኑ ሞገስ አገኘች ንጉም በእጁ የነበረውን የወርቁን ዘንግ ለአስቴር ዘረጋላት አስቴርም ቀርባ የዘንጉን ጫፍ ነካች» አስቴ ይህ በሞገስ ምክንያት የተዘረጋላት ዘንግ ነበር የእግዚአብሔርን ሕዝብ ጠላት ፅቅድ በመገልበጥ አይሁዳውያንን ከሞት አዋጅ ለማዳንና የአምላኳን ፈቃድ ለመፈጸም ያስቻላት እንግዲህ የእግዚአብሔር ሞገስ ተቀባይነት ስለሚሰጠን ወደ ግባችን ወይም ወደ እግዚአብሔር ዓላማ ያደርሰናል ከዚያም በላይ ሥልጣንን ስለሚያስጨብጠን ተልዕኳችንን ከመፈጸምም በላይ የጠላትን ሥራ በማፍረስ ለዘለቄታ ዕንቅፋትን ከመንገድ ለማስወገድ ያስችለናል ብፅዕናን አግኝተሻል የእግዚአብሔር ሞገስ በሕይወታችን መሥራት የሚጀምረው መልካምነቱን በማጉላላት ነው የእርሱ መልካምነት ምሕረትና ጸጋ በሕይወታችን ውስጥ በጣም ሲጐላ ከድካማችንና ከውስንነታችን በላይ ያደርገናል በእርሱ ዘንድ ተቀባይነትን ስለሚሰጠን በፍቅሩ እንረካለን በዚህ ፍቅር ውስጥ ሆነን ነው ምን ያህል እንደ ተባረክን የምንገነዘበው ውበት ግርማና ሞገስ የሚያበዛልን ይህ ብፅዕና ነው ማርያም ፌ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል ሉቃ ያለችው ይህን ስላስተዋለች ይሆናል ይህ ብፅዕና ነው መለኮታዊ ባርኮትን በምድር ላይ ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ እንዲገለጽ የሚያደርገው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስናደርግ በረከት እንሆናለን አግዚአብሔር አብርፃምን ሲጠራው ተባርኮ በረከት እንዲሆን ነበር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቃል ኪዳኑ ደም አማካይነት ፈቃዱን ለመፈጸም ሁሉም ራሳቸውን የሰጡት ተባርከው በረከት ለመሆን ነው እንግዲህ የእግዚአብሔር ሞገስ የበረከት ተቀባይና ሰጪ ወይም አስተላላፊ ያደርገናል ይህም ፈቃዱን በመፈጸም በረከት ለመሆን እንጂ ለአገልግሎት ብቻ ብለን እንደማናገለግል ያሳያል ፈ ከብረሻል ይህ ሞገስ በእግዚአብሔር ዓይን ተቀባይነትን ማግኘት መወደድን መልካምነቱን መለማመድንና ለበረከት መሆን ብቻ ሳይሆን መከበርንም ያመጣል የእግዚአብሔር ሞገስ በሰው ላይ ሲመጣ ሰው የሚከበረው አክብሩኝ ወይም አንቱ በሉኝ ብሎ አይደለም።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF


Download options | Convert to Pdf | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact